Logo
Getu Temesgen
የልጇን የእናትነት ህልም እውን ያደረገችው እናት!
#ethiopia | በ61 ዓመቷ የልጅ ልጅዋን በማኅፀኗ አርግዛ የልጇን የእናትነት ሕልም እውን ያደረገችው እናት መነጋገርያ ሆናለች።

አንዲት እናት ለልጇ ልትሰጣት የምትችለው ትልቁ ስጦታ ምን ሊሆን ይችላል?

በቺካጎ የምትኖረው ክሪስቲን ኬሲ ለአመታት ልጅ ለመውለድ ጥረት ስታደርግ ለቆየችው ልጇ ሳራ ኮነል ያደረገችው ተአምር እውነተኛ የእናትነት ፍቅርን ምን እንደሆነ አሳይቷል።

ሳራ እና ባለቤቷ ልጅ ማግኘት ተስኗቸው በብዙ ፈተና ውስጥ ካለፉ በኋላ ክሪስቲን የልጇን ጭንቀትና ህመም ተረድታ ህፃኑን በማኅፀኗ አርግዛ ለመውለድ ወሰነች።

የሕክምና ባለሙያዎች የሳራን እንቁላል እና የባለቤቷን ዘር በማቀላቀል በቤተ ሙከራ ፅንሱን ካዘጋጁ በኋላ ክሪስቲን የወሊድ ማቆሚያ እድሜዋ ካለፈች በኋላም ቢሆን ለዕርግዝና የሚያዘጋጅ የሆርሞን ሕክምና እንድትወስድ አደረጉ።

በ61 ዓመቷ እርግዝናውን በሙሉ ጤንነት በመጨረስ በቀዶ ሕክምና የልጅ ልጅዋን በሰላም ተገላግላለች።

ለሳራ ይህ አጋጣሚ ለዓመታት ስትመኘው የነበረውን ልጅ የማቀፍ ህልሟን እውን ያደረገ ሲሆን ለእናቷ ደግሞ በ61 ዓመቷ ለልጇ ልትሰጣት የምትችለውን ትልቁን የእናትነት ስጦታ ያበረከተችበት ታሪካዊ አጋጣሚ ሆኗል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #motherlylove #inspiration #surrogacyjourney #familyfirst #amazingstories

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.