Logo
Getu Temesgen
ቲክቶክ ለአሜሪካ ብቻ የሚሆን አዲስ አፕሊኬሽን እያዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ
#ethiopia | በአሜሪካ መንግስት እገዳ የተጣለበት ቲክ ቶክ አዲስ አማራጭ ይዞ እየመጣ እንደሆነ ዘገባዎች ገልፀዋል፡፡ እንደዘገባዎቹ ከሆነ ቲክ ቶክ ለአሜሪካዊያን ብቻ የሚሆን አዲስ አፕሊኬሽን ሰርቶ አጠናቋል፡፡

በቲክ ቶክ ላይ የተጣለውን እገዳ ፕሬዝደንት ትራምፕ ስልጣናቸውን በመጠቀም በተደጋጋሚ ያራዘሙት ሲሆን አሁን የተሰጠው ጊዜ ገደብ እስከ ሴፕቴምበር 17 ድረስ የሚቆይ ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት ፕሬዝደንት ትራምፕ ቲክቶክን የሚገዛ አሜሪካዊ ባለሀብት ማግኘታቸውን ገልፀው ውሉ በያዝነው ሳምንት ይፈፀማል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልፀው ነበር፡፡

ነገር ግን የቲክቶክ ባለቤት የሆነው ባይት ዳንስ ለዚህ የሚሆን አዲስ አማራጭ ይዞ እየመጣ መሆኑን ዘገባዎቹ አስረድተዋል፡፡

ይህ ደግሞ ሌላ ተመሳሳይ አፕሊኬሽን መስራት ሲሆን አዲሱ አፕሊኬሽን ከሴፕቴምበር 3 ጀምሮ በአሜሪካ በሚገኙ የአፕሊኬሽን ስቶሮች ውስጥ እንደሚጫን ተገልጿል፡፡ እስካሁን ባለው መረጃ አዲሱ የቲክ ቶክ አፕሊኬሽን ስሙ ‹‹ኤም ቱ›› የሚባል እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ #zehabesha

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.