ለመስቀል በዓል ተጓዦች መልካም ዜና
#ethiopia | የመስቀል ተጓዦች ከአላስፈላጊ የትራንስፖርት ዋጋ ጭማሪና ብዝበዛ ነፃ በሆነ መልኩ በተተመነላቸው ህጋዊ ታሪፍ ብቻ እንዲስተናገዱ ይደረጋል ተብሏል።
የመስቀል በዓል ተጓዦች ያለምንም እንግልት፣ የትራንስፖርት እጥረትና የመንገድ መጨናነቅ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በድምቀት ማክበር እንዲችሉ የጉራጌ ዞን እና በኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በቅንጅት መስራት መጀመራቸውን አስታወቁ።
በበዓሉ ወቅት የሚኖረውን ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት ታሳቢ በማድረግ አደጋዎችን ለመከላከል የሁለቱ ዞኖች የቀቤና የወሊሶ እና የሸገር ከተማ የትራፊክ ፖሊሶችና የፀጥታ አካላት በጥምረት ይሰራሉ።
ለልማትም ሆነ ለሌላ ጉዳይ በሚል ሰበብ ከተጓዦች ላይ የሚሰበሰብ ምንም አይነት መዋጮ ወይም ህገወጥ ክፍያ አይኖርም ሲሉ በጋራ ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል።
ተጓዦች በሰላም ገብተው እንዲመለሱ የፀጥታው ዘርፍ ሌት ተቀን ይሰራል ብለዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #የጉራጌዞን #ኦሮሚያክልል #ደቡብምዕራብሸዋዞን #መስቀልበአል

1 month ago