Logo
Getu Temesgen
"ከአምባሳደር እስከ ጅቡቲ ያልተጠናቀቀው የሰርጉአለም ህይወት!"

*በወጣትነቱ የተለየን የአምባሳደሩ ኩሩ ሰርጉአለም ተገኝ ሲታወስ!
#ethiopia | በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ስማቸው በጉልህ ከሚጠቀሱ ነገር ግን የህይወት መንገዳቸው በወጣትነት እድሜያቸው በአሳዛኝ ሁኔታ ከተቀጩ ድምፃውያን መካከል አንዱ ሰርጉአለም ተገኝ ነው።

የሙዚቃ አፍቃሪያን ልብ ውስጥ በሰራቸው ጥቂት ግን ጥልቅ ስራዎቹ ትልቅ ቦታ ማግኘት የቻለው ይህ ወጣት አርቲስት ህይወቱ እና የጥበብ ጉዞው አጭርና ያልተጠናቀቀ ህልም ሆኖ አልፏል።

ሰርጉአለም ተገኝ የተወለደውና ያደገው የበርካታ ታዋቂ አርቲስቶች መፍለቂያ በሆነችው አዲስ አበባ ልዩ ስሙ አምባሳደር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

ገና በለጋ እድሜው ለሙዚቃ የነበረው ፍቅር እና ስጦታ ግልጽ ሆኖ ይታይ ነበር።

ህይወት ወደ ስደት በገፋችው ወቅት በጅቡቲ ይኖር በነበረበት ጊዜ በወቅቱ ስመጥር በነበረው "ምኒልክ የምሽት ክበብ" ውስጥ በመስራት ሙያውን ሀ ብሎ ጀመረ።

ያ መድረክ ለቀጣይ ትልቅ የስኬት መንገዱ መሰረት ሆነው።

ወደ ሀገር ቤቱ ከተመለሰ በኋላ በወቅቱ ከነበሩት አንጋፋ እና ድንቅ የሙዚቃ አቀናባሪዎች አንዱ ከሆነው ከሙሉጌታ አባተ ጋር በመሆን ተቆጣጠረችኝ የተሰኘውን የመጀመሪያ የግል አልበሙን ለአድማጮች አቀረበ።

አልበሙ በብዙኃኑ ዘንድ አዎንታዊ ምላሽን ያገኘ ሲሆን ሰርጉአለምን በኢትዮጵያ ሙዚቃ መድረክ ላይ በጉልህ አስተዋወቀው።

የስኬት መንገዱን የቀጠለው ሰርጉአለም በወቅቱ ዝነኛ ከነበሩት ከዳዊት መለሰ እና ኅብስት ጥሩነህ ጋር በመሆን የጋራ አልበም በመስራት አድናቆቱን አጎናጸፈ።

ከዚህ በተጨማሪም በወቅቱ የሙዚቃ አፍቃሪዎች መሰብሰቢያ በነበሩት በሜጋ አምፊ ቲያትር እና በአይቤክስ ሆቴል የመድረክ ድምፃዊ ሆኖ በመስራት አድማጮቹን በልዩ ድምፁ ያዝናና ነበር።

ከዚህ በተጨማሪም በወቅቱ የሙዚቃ አፍቃሪዎች መሰብሰቢያ በነበሩት በሜጋ አምፊ ቲያትር እና በአይቤክስ ሆቴል ድምፃዊ ሆኖ በመስራት አድማጮቹን በልዩ ድምፁ ያዝናና ነበር።

ሁለተኛ እና የመጨረሻ የግል አልበሙ የሆነው "ሳላያት አመሸሁ" ሲወጣ የሰርጉአለም የሙዚቃ ህይወት ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ ነበር።

የአልበሙ መጠሪያ የሆነችው ዜማ እና ሌሎችም በውስጡ የተካተቱት ስራዎች የብዙዎችን ልብ የነኩ የኢትዮጵያ ሬዲዮን አየር ነተቆጣጠረ ሙዚቃ ነበር።

ይህ አልበም የሰርጉአለምን የዜማ አጣጣል የድምፅ ውበት እና የጥበብ ብስለት አጉልቶ ያሳየ ታላቅ ስራ እንደሆነ እሱን የሚያውቁ የሙያ አጋሮቹ ይመሰክሩለታል።

ሰርጉአለም ለሦስተኛ አልበሙ ዝግጅት ማድረግ ጀምሮ ነበር።

ለቀጣዩ ስራው የሚሆኑ ድንቅ ዜማዎች እና ግጥሞችን አሰባስቦ ወደ ስቱዲዮ በመግባት የድምፅ ቀረፃ ለመጀመር ደፋ ቀና በሚልበት ሰአት ነበር ባደረበት ህመም በወጣትነቱ ህይወቱ ያለፈው።

ሰርጉአለም የጀመረው ሦስተኛ አልበም ሳይጨርስ በወጣትነቱ ከዚህ አለም በሞት ቢለይም ጥሎት ያለፈው ስራው ግን በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ሁሌም ሲታወስ ይኖራል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #ኢትዮጵያ #ሰርጉአለምተገኝ #ሙዚቃ #ጥበብ #አምባሳደር #ሳላያትአመሸሁ #ተቆጣጠረችኝ

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.