Logo
Getu Temesgen
የታዋቂዋ ጋዜጠኛ ጽዮን
ግርማ የምስጋና ቃል
#ethiopia | የዘመናት ባለቤት እግዚአብሔር፣ በቸርነቱ ተጨማሪ ዓመት አድሎኝ ዕድሜን ስለጨመረልኝ፣ ክብርና ምስጋና ይድረሰው።

ላለፉት ብዙ ዓመታት ልደቴን ለማክበር አንድም ቀን ተዘናግቶ የማያውቀውን፣ ከእግዚአብሔር የተሰጠኝን ውዱን ባለቤቴን መርሥዬን Merseahazen Abel Tsegaye፣ ለማመስገን የሚመጥን ቃል ስለሌለኝ ፈጣሪ እንዲጠብቀው ብቻ እጸልያለኹ።

“እርጅና እየመጣ ነው፤ ኑሮም እየተወደደ ነው” በሚል ሰበብ ከፈንጠዝያ ለመሸሽ ያደረኩትን ጥረት አክሽፋ፣ አሳድዳ ልደቴን ያከበረችውን ውዷና የክቷ ሊሊዬን Simegnish Yekoye Or Lily ምን እልሻለኹ! ሰው እንዴት ይኽን ኹሉ ዓመት አንድ ዓይነት ሰው ኾኖ ይቆያል? ❤️

እግዚአብሔር ለእኔ እንደሰጠኝ ፣ እንደዚች ያለች እኅት ይስጣችኹ። ዋናው ነገር ጤና ነውና ፈጣሪ ጤናሽን ይጠብቅልሽ። እወድሻለኹ ❤️

ሰብልዬዋSeble Wores፣ አይገርምም? አብረን አረጀን እኮ! ለእኅትነትሽ፣ ለጓደኝነትሽና ለቤተሰብነታችን ኹሌም እግዚአብሔርን አመሰግነዋለኹ። በምንም ነገር ለማይናወጠው፣ በጽናት ለቆየው ቤተሰባዊነታችን ፈጣሪ ይመስገን። ለሌሎችም ምሳሌ የምንኾንበትን ዕድል ይስጠን። እወድሻለኹ። በቀይ አበባ ቀኔን እንዳፈካሽው፣ ሕይወትሽም እንዲኹ ፍክት ይበል። ❤️
ጉስታቭ፣ አሜንዬ፣ ዊንትዬ፣ ግሬስ Alheri Hisgrace (My dear sister, how is it that you never forget my birthday?) የልደት ቀኔን አለመርሳታችኹ ኹሌም ግርም ይለኛል። የኔ መቅዲ Mekdes Worknehኹሌም ከፍ በይ!

መጪው ዘመኔ የተቃና እንዲኾን በፍቅር የተመኛችኹልኝን ውድ ቤተሰቦቼን፣ ወዳጆቼንና የፌስቡክ ጓደኞቼን እጅግ አድርጌ አመሰግናለኹ።

እግዚአብሔር ተርፎ ከሚቀረው ዕድሜ ሳይነፍገን፣ በፍቅርና በመተሳሰብ አብሮ ያቆየን እያልኹ፣ በድጋሚ ኹላችኹንም ከልቤ አመሰግናለኹ።

ያክብርልኝ!

Tsion Girma-
#ጽዮንግርማ #ጋዜጠኛ #ልደት #ምስጋና #tsiongirma #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.