“ባልሽ ወይም ፍቅረኛሽ ይኼንን የመሰለ 2025 ሞዴል መኪና ካልገዛልሽ በአናቱ ይተከል” የሚል ይዘት ያለው ማስታወቂያ ሰሞኑን Tik Tok ላይ በተደጋጋሚ ስመለከት እና ስታዘብ ነበር:: እንደዚህ አይነት መልዕክት ያላቸው ማስታወቂያ በብዙዎች ዕይታ ቀልድ ወይም ትኩረት ሳቢ ቢመስሉም በሙያዊ ዕይታ ሲቃኙ ግን በርካታ ዘላቂ ችግር አሏቸው::
የቲክ ቶክ አልጎሪዝም የሚሰራው በሰዎች ምላሽ (Engagement) ላይ ተመስርቶ በመሆኑ አወዛጋቢ ወይም ስሜት ቀስቃሽ ይዘቶች ብዙ ጊዜ ፈጣን (Like, Comment, Share) ምላሽ ያስገኛሉ። ለዚህም ሲባል ብዙ ጊዜ ኮንቴንት ክሬተሮች እንደዚህ አይነት ShoCk Value ያላቸው Risky Viral Marketing Strategy ይመርጣሉ:: ምክንያቱም ማስታወቂያቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ቫይራል ወጥቶ ከፍተኛ ትኩረት እንዲያገኙ ስለሚፈለግ::
ነገር ግን! ነገር ግን! ነገር ግን!
ትልልቅ ስም ያሏቸው Real Estate ቤት አልሚዎች እና የመኪና አስመጪ ኩባንያዎች ማስታወቂያቸው ቫይራል እንዲሆንላቸው በሚል ይኼንን Shock Value/ Risky Viral ማርኬት ስልት ሲጠቀሙት ውጤቱ ጎጂ እና አክሳሪ ነው የሚሆነው:: የንግዳቸውንም መልካም ስም (Brand Image) በእጅጉ ይሸረሽረዋል:: ገደልም ሊከተው ይችላል::
“ፍቅረኛሽ ወይም ባልሽ ይኼንን ካልገዛልሽ በአናቱ ይተከል” የሚል መልዕክትን በማስታወቂያ ማንፀባረቅ ኩባንያው ማኅበራዊ ሃላፊነት የጎደለው (Socially Irresponsible) ፣ አድሎአዊ (Discriminatory) እና ስነ-ምግባር የጎደለው ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። 'Coz ዘመናዊ ደንበኞች ከንግድ ተቋማት የላቀ ማኅበራዊ ሃላፊነትን ስለሚጠብቁ::
Thus, እንዲህ ዓይነት ማስታወቂያዎች ከቀላል ቀልድና ትኩረት ሳቢነት ባለፈ በህብረተሰቡ ስነ-ልቦናዊ ጤንነት ፣ በማኅበራዊ ግንኙነቶች እና በንግድ ሥነ-ምግባር ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ናቸው::
ከእነዚህ በተቃራኒ ደግሞ ከስር በፎቶ የምትመለከቷት ለሽያጭ እና ማስታወቂያ ኮንቴንት ክሬተሮች ምሳሌ መሆን ስለምትችል ልጅ የተወሰነ ነገር ልል ወደድኹ:: ይህች ልጅ “Mekina Gebeya / መኪና ገበያ” በሚል የቲክ ቶክ አካውንት ገፅ ላይ የሽያጭ እና ማስታወቂያ ኮንቴንት ክሬተር ናት:: የምትጠቀማቸው ስልቶች ለሁሉም የዲጂታል ማርኬተሮች ትልቅ ምሳሌ መሆን ይችላል! የእሷ ("መኪና ገበያ") አካሄድ ደንበኛን በማስተማር ፣ እሴት በመጨመር እና እውነተኛ መረጃ በመስጠት ላይ ያተኮረ ነው። ይህ አይነቱ አቀራረብ ደንበኛች Trust Build እንዲያደርጉ በማድረግ ለድርጅቱ የረዥም ጊዜ ስኬትን ማጎናፀፍ ይችላል!
በመጨረሻም!
“ባልሽ ይኬን ይሄን መኪና ካልገዛልሽ በአናቱ ይተከል” የሚሉ አይነት Risky Viral Marketing ማስታወቂያዎች ለአጭር ጊዜ ቫይራልነትን ቢያገኙም በመጨረሻ ግን ለገበያ ሰሪው ትርፍ ከማምጣት ይልቅ የረዥም ጊዜ አደጋን ይደግንበታል። የደንበኞችን ታማኝነት ያበላሽበታል:: ለንግድ ስሙም ማኅበራዊ ሃላፊነት የጎደለው ድርጅት ተደርገው እንዲታይ ያደርገዋል!
እውነተኛው የማስታወቂያ ጥበብ ትኩረትን በመሳብ ሳይሆን ፣ እሴት በመፍጠር ፣ እምነት በመገንባት እና ዘላቂ ግንኙነት በመመሥረት ላይ ነው🙏 It's about creating value, building trust, and fostering lasting relationships.
መኪና ገበያ ግን Truly Nailed it 🤝
Via: ዮአኪን በቀለ

1 year ago