Logo
Getu Temesgen
"ከሀገሬ አልኮበለልኩም፤ በቀረችኝ እድሜዬ ሀገሬን ማገልገል ነው የምፈልገው" — ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
#​Ethiopia | የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ከሀገር ኮበለሉ ተብሎ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ይሰራጭ የነበረውን መረጃ ሙሉ በሙሉ በማስተባበል ዛሬ በአካል ተገኝተው ምላሽ ሰጡ።

ኮሚሽነሩ በሰጡት ማብራሪያ "እኔ ከሀገሬ አልኮበለልኩም፤ አልሸሸሁም፤ በቀረችኝ አጭር እድሜዬም ሀገሬን ነው ማገልገል የምፈልገው" ሲሉ የተዛመተውን ሀሰተኛ ወሬ አክሽፈውታል።

​ባለፉት ጥቂት ቀናት ፕሮፌሰር መስፍን ሀገር ጥለው መውጣታቸውን የሚገልጹ ዘገባዎች በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችና መገናኛ ብዙሃን ሲናፈሱ መቆየታቸው ይታወሳል።

​የፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በዛሬው ዕለት በአካል መገኘትና የሰጡት የማስረገጫ ቃል ባለፉት ቀናት ሲናፈሱ የነበሩትን ውዥንብሮች በሙሉ የሻረ ሲሆን እሳቸውም የተጣለባቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት በመወጣት ላይ እንደሚገኙ ያረጋገጠ ሆኗል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.