"በተቀናጀ ዐቅም ተግተን ከሠራን፤ ብልጽግና ሕይወት፣ ድህነት ታሪክ ይሆናል" - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
********************
ለም አፈር፣ ንጹሕ ውኃና ሥራ ወዳድ ሕዝብ ባለበት ምድር፣ በተቀናጀ ዐቅም ተግተን ከሠራን - ብልጽግና ሕይወት፣ ድህነት ታሪክ ይሆናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ባጋሩት መልዕክት፥ የሐይቅ ዙሪያ አርሶ አደሮች መሬት እና እርሻቸውን ከጫት ወደ አትክልት እና ፍራፍሬ ክላስተር ማሸጋገራቸውን ጠቅሰዋል።
በዚህም አርሶ አደሮቹ የአካባቢን አንጻራዊ የልማት ጉልበት መለየት እና ወደ አትራፊ እና ዘላቂ የግብርና ጎዳና መሸጋገር ይገባል የሚለውን ሀገራዊ መርህ እና ስምሪት ተግብረው አሳይተዋል ሲሉ ገልጸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ምርቃት ላይ ባስተላለፉት ታሪካዊ መልዕክት፣ "ሐይቅ የታሪክ ብቻ ሳይሆን የፍራፍሬ ልማት፣ የተትረፈረፈ ምርት፣ የውበትና የጥጋብ ሥፍራ መሆን አለባት" ብለው እንደነበር አስታውሰዋል።
ዛሬ የርሳቸው ቃል ፍሬ አፍርቶ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን፣ ተሁለደሬ ወረዳ የጎበያ ቀበሌ በአትክልት እና ፍራፍሬ ክላስተር ተሸፍኗል፤ ይህ የልማት ትጋት ኢትዮጵያ ለጀመረችው የምግብ ሉዓላዊነት ተደማሪ ጥሪት እና ወረት ነው ብለዋል።
መንግሥት ለዚህ ልማት አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል፤ ለም አፈር፣ ንጹሕ ውኃና ሥራ ወዳድ ሕዝብ ባለበት ምድር፣ በተቀናጀ ዐቅም ተግተን ከሠራን - ብልጽግና ሕይወት፣ ድህነት ታሪክ ይሆናል ነው ያሉት።
#ethiopia #horticulture #amhararegion #ebc

2 months ago