የሀገር ምሰሶ፣ የሰላም ዘብ እና የሕልውና ዋስትና፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት
******************
የሀገርን ከፍታ የሚያስጠብቅ፣ ዳር ድንበርን የሚያስከብር እና እልፍ ተልዕኮዎችን የሚወጣ ጦር መገንባት የሀገርን ምሰሶ በጠነከረ ዐለት ላይ እንደማነጽ ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ዛሬ የደረሰበት የላቀ ቁመና ከወታደራዊ አቅም ያለፈ፣ እጅግ ጥልቅ የሆነ ሀገራዊና ቀጣናዊ ትርጉም ያለው የሕልውናችን ማረጋገጫ ነው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጀግንነት የዛሬ ክስተት ሳይሆን ከጥንት እስከ ዛሬ ያልነጠፈ ነው። አባቶቻችን በጽናት እና በሀገር ፍቅር ስሜት ወራሪዎችን ድል ነስተው ነፃነቷ የተከበረ ሀገር አቆይተውልናል። ይህ አኩሪ የጀግንነት ወኔ ዛሬም ከዘመናዊ ወታደራዊ ሳይንስ ጋር ተዳምሮ የማይበገር የብረት አጥር ፈጥሯል።
የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንዳሉት፣ የኢትዮጵያ የላቀ ወታደራዊ አቅም እና የማይበገር ቁመና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በግልጽ እየታየ ይገኛል።
መከላከያ ሠራዊታችን የደረሰበት የቴክኖሎጂ፣ የስልት እና የትጥቅ ዘመናዊነት የብዙዎችን ትኩረት ከሚስቡ ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል አንዱ ሲሆን፣ አስደናቂ ብቃት እና ጀግንነትን ተላብሶ በማንኛውም አውድ ውስጥ ተልዕኮውን በከፍተኛ ውጤታማነት ማሳካት የሚችል እጅግ የላቀ ኃይል ሆኖ ተገንብቷል።
አየር ወለድ፣ ኮማንዶ እና ፀረ-ሽብር ክፍሎችን ያካተተው ኃይል በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ወደር ከማይገኝላቸው የልዩ ዘመቻ ኃይሎች ቀዳሚው መሆኑ ተመስክሮለታል። እጅግ ውስብስብ የሆኑ የፈጣን ምላሽ እርምጃዎችን፣ ኦፕሬሽኖችን እና ከፍተኛ ቅንጅት የሚጠይቁ የተኩስ ልምምዶችን ለማከናወን ያለው ዝግጁነት፣ እንዲሁም የውኃ ላይ ኮማንዶዎች ከአየር ወለድ እና ከምድር ጦር ጋር ያላቸው የላቀ ቅንጅት የኢትዮጵያ ወታደራዊ አቅም እጅግ ከፍ እያለ መምጣቱን ያሳያል።
ይህ የላቀ አቅም የትኛውንም ዓይነት ትንኮሳዎችን አስቀድሞ ለማክሸፍና ለማስቀረት ሠራዊቱን ሙሉ በሙሉ ዝግጁ አድርጎታል። የሀገርን ሉዓላዊነት ለሚዳፈሩ፣ ዳር ድንበርን ጥሰው ለሚገቡ የትኛውም ዓይነት ወረራዎችን እና የሚቃጡ ወታደራዊ ጥቃቶችን በፅናት ለመመከት እና አጥፊዎችን ዳግም በማያንሰራሩበት ሁኔታ በቂ እና አስተማሪ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል አስተማማኝ አቅም ተገንብቷል።
ይህ የመከላከያ ሠራዊታችን ሁለንተናዊ ቁመና እና የውጊያ ዝግጁነቱ ለጠላቶች አስደንጋጭ፣ ለወዳጆች ደግሞ ተስፋ ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ግዙፍ አቅም የገነባው ለጦርነት ሳይሆን ሰላምን ለማረጋገጥ እና ለማስጠበቅ ነው። ሠራዊቱ የሰላም ዘብ እና ለሰላም የሚሠራ ተቋም በመሆኑ፣ በሀገር ውስጥ ሕግን በማስከበር ሕዝባዊ ሰላምን ከማስፈን ባሻገር፣ በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ግንባር ቀደም ሚናውን የሚወጣ ነው።
ሠራዊቱ የኢትዮጵያን የሰላም አምባሳደርነት በተግባር የሚያሳይ፣ ሕዝብን የሚያከብር እና ለቀጣናው መረጋጋት አዎንታዊ አስተዋጽኦ የሚያበረክት አንጸባራቂ ኮከብ ነው።
ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ግዙፍ የወታደራዊ አቅም ግንባታ መገንዘብ የሚቻለው ሌላው እጅግ ወሳኝ መልዕክት፣ ሀገራችን በቀጣናው በተለይም በባሕር በር ጥያቄዋ ላይ ቀጥተኛ እና ሉዓላዊ መብቷን ለማረጋገጥ ያላትን የማይናወጥ አቋም ነው።
ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት የየብስ እስረኛነት ሁኔታ ታሪካዊ ስህተት መሆኑን እና ይህንንም ከእንግዲህ ዝም ብላ እንደማትቀበለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በግልጽ መናገራቸው ይታወቃል።
ከ130 ሚሊዮን በላይ እጅግ ግዙፍ እና በፍጥነት እያደገ ያለ ሕዝብ ያላት ሀገር የኢኮኖሚ እና የደህንነት ሕልውናዋን ለማረጋገጥ ቀጥተኛ የባሕር በር እና የዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ትስስር ግድ ይላታል። በመደመር እሳቤ የተቃኘው ይህ የባሕር በር ጥያቄ የሌሎችን ሉዓላዊነት የመዳፈር ጉዳይ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕልውና፣ ብልጽግና እና ቀጣይነት የሚረጋገጥበት መሠረታዊ መብት ነው። በቅርብ ጊዜያት በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ የተለያዩ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት መጨመሩ እና የኢትዮጵያን ተጽዕኖ ለማዳከም የሚሞክሩ አዳዲስ ትብብሮች መፈጠራቸው ሲታሰብ፣ ይህ ጠንካራ አቋም እና ወታደራዊ ዝግጁነት ፍጹም ወቅታዊ እና አስፈላጊ ነው።
ሠራዊቱ በአንድ ክንፉ በዓላማ፡ በሌላው ደግሞ በዲሲፕሊን የተገነባ መሆኑ በሂደቱ የተረጋገጠ እውነት ነው። የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በአንድ ወቅት እንዳብራሩት፣ ከ2010 ዓ.ም የለውጥ ሂደት በኋላ ሠራዊቱ ከማንኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት ነጻ የሆነ እና ሀገራዊ ራዕይ ያነገበ ተቋም ሆኖ ዳግም ተዋቅሯል። በዲስፕሊን የታነጸው ይህ ሠራዊት በስታፍ ኮሌጅ ከሚያገኘው የንድፈ ሀሳብ ትምህርት በተጓዳኝ በውጊያ ሂደት ውስጥ በተግባር የተፈተነ ጠንካራ የመከላከያ ኃይል ሆኖ ተገንብቷል።
ስለሆነም የመከላከያ ሠራዊቱ መዋቅራዊ ማሻሻያዎች እና የባሕር በር ለማግኘት እየተከናወኑ ያሉ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ሥራዎች ነጠላ ክስተቶች ሳይሆኑ የተቀናጀ ሀገራዊ ስትራቴጂ አካል ናቸው። ጀግንነትን ከዘመናዊ አቅም፣ ጥብቅ ዲሲፕሊን እና ሰላም አስከባሪነት ጋር አዋህዶ የያዘው መከላከያ ሠራዊታችን በማንኛውም ጊዜ፣ ቦታ እና ሁኔታ ሁለንተናዊ ዝግጁነቱን አረጋግጦ ኢትዮጵያን ይጠብቃታል።
በበረከት ሽመልስ
#ethiopia #defense #soverignty #ebc

2 months ago