Logo
Getu Temesgen
ቻድ ኢትዮጵያውያን ያለ ምንም የቪዛ መስፈርት ወደ ሀገሯ እንዲገቡ ፈቀደች

መላው አፍሪካውያንም የዚህ እድል ተጠቃሚዎች ናቸው
#ethiopia | ቻድ ከፈረንጆቹ አዲስ አመት ጀምሮ ለማንኛውም የአፍሪካ ሀገር ዜጋ ያለ ምንም የቪዛ መስፈርት ወደ ሀገሯ መግባት የሚያስችል አዲስ መመሪያ ይፋ አደረገች።

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ ይፋ ባደረጉት በዚህ አዲስ ፖሊሲ መሰረት፣ ህጋዊ ፓስፖርት ያለው ማንኛውም የአፍሪካ ሀገር ዜጋ ቅድመ ቪዛ ሳያስፈልገው በቀጥታ ወደ ቻድ መግባትና መንቀሳቀስ እንደሚችል ተገልጿል።

​ይህ ውሳኔ ቻድ ከአህጉራዊ ትስስርና ከዜጎች ነፃ እንቅስቃሴ አንጻር ትልቅ እርምጃ እንድትወስድ ያደረጋት ሲሆን ሀገሪቷም ከጋና፣ ቶጎ፣ ኮንጎ፣ ሩዋንዳ፣ ቤኒን፣ ሲሼልስ እና ጋምቢያ በመቀጠል ለአህጉሩ ዜጎች የቪዛ ገደብን ሙሉ በሙሉ ያነሳች 8ኛዋ የአፍሪካ ሀገር ያደርጋታል።

ይህ ውሳኔ የአፍሪካውያንን እርስ በእርስ የመቀራረብና የመንቀሳቀስ ዕድል የሚያጠናክር ከመሆኑም በላይ፣ አንዲት አፍሪካ በመፍጠር ትልም ላይ ትልቁ ጡብ ተቀምጧል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.