የሚሊየኖች እጆች ኃይል
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብራችን ከችግኝ ተከላ የላቀ የጋራ መንፈስ መነቃቃትን ፈጥሮልናል።
አፈርና ላባችንን አዋህደን በአንድነት በመቆም፣ ታሪካዊና የማይበጠስ ጠንካራ ማህበራዊ ትስስርን በሀገራችን መፍጠር ችለናል።
ይህ ደማቅ ንቅናቄያችን በልባችን ጥልቅ የሀገር ባለቤትነት ስሜትን አትሟል።
እያንዳንዳችን የተከልነው ችግኝ ሀገራችንን በጋራ የመገንባት፣ የመንከባከብና ለነገው ትውልድ በክብር የማስተላለፍ የዜግነት ግዴታችንን በተግባር ያረጋገጥንበት ነው።
ልዩነቶቻችንን ወደ ጎን ትተን በጋራ ዓላማ መሰለፋችን፣ ህብረታችንን ከምንግዜውም በላይ አጠናክሮታል። ይህም ከመሬታችን ጋር ያቆራኘን፣ ከተመልካችነት ወደ እውነተኛ የተግባር ባለቤትነት ያሸጋገረን ታላቅ ድላችን ነው።

3 days ago