ለትውልድ የሚሻገር አኩሪ ታሪክ የሚጻፍበት የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አማካኝነት የደን ሀብቷን ለማሳደግ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎችን የመቋቋም ጉዞ ዛሬ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚጠቀስ አርአያነት ያለው ተግባር ሆኗል።
ይህ በየዓመቱ በከፍተኛ ህዝባዊ ንቅናቄ የሚታወቀው መርሐ ግብር የተፈጥሮ ሚዛንን በመጠበቅ የወደፊት ትውልድ ተስፋን በጽኑ መሠረት ላይ የሚያንጽ ብሔራዊ ንቅናቄ ነው።
በየዓመቱ የሚካሄደው የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ሚሊየኖች ከዳር እስከ ዳር በዝናብና በብርድ ሳይበገሩ በመዝመት ምድርን የሚያለመልሙበት መድረክ ሆኗል።
ነገ ማለዳ በይፋ ለሚጀመረው የዘንድሮው የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እንደ ሀገር አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት፥ የነገው መርሐ ግብር የኢትዮጵያውያን ክንድ ተባብሮ፣ በአንድ ጀንበር 800 ሚሊየን ችግኞችን በመትከል ሌላ ታሪክ የምንሰራበት ነው ብለዋል፡፡
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የደን ሽፋንን በእጥፍ ከማሳደግ ባሻገር፣ የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል፣ የውሃ አካላትን ለማበልጸግና የግብርና ምርታማነትን በዘላቂነት ለማሳደግ የጎላ ሚና ይጫወታል።
ከዚሁ ጎን ለጎን የሚተከሉት ችግኞች የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጡ የፍራፍሬ ተክሎች እንዲሁም የኢኮኖሚ ጥቅም የሚሰጡ የዛፍ ዝርያዎችን ያካተቱ በመሆናቸው ለሀገራችን የኢኮኖሚ እድገት አዎንታዊ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ።
ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የችግኝ ተከላ ዘመቻዎች ሕዝቡ ባደረገው ከፍተኛ ተሳትፎ መርሐ ግብሩ ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ የሀገራዊ አንድነት መገለጫ መሆን ችሏል።
800 ሚሊየን ችግኞችን በአንድ ጀንበር የመትከል ዘመቻው ለኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት፣ የአየር ንብረት ተጽዕኖን ለመቋቋም፣ ለምግብ ዋስትናና ለትውልድ ተሻጋሪ የተፈጥሮ ሀብት ግንባታ የሚያበረክተውን ድርሻ የበለጠ የሚያጎላ ነው።
እያንዳንዱ ዜጋ ከጫፍ እስከ ጫፍ በመነሳት የድርሻውን እንዲወጣ የሚጠይቀው ይህ ሀገራዊ ጥሪ በከተማም ሆነ በገጠር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በማለዳው በመውጣት የራሳቸውን ታሪካዊ ዐሻራ እንዲያኖሩ በር የከፈተ ሆኗል።
ይህ እቅድ የቁጥር ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የጽናት፣ የህብረትና የልማት ታላቅ መገለጫ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን በተፈጥሮ ሀብታቸው ላይ አዲስ ሕይወት የሚዘሩበት፣ ለቀጣዩ ትውልድ ለም እና አረንጓዴ ሀገር የሚያስረክቡበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው።
ችግኞችን ከመትከል ባለፈ የመንከባከብና የመጠበቅ ባሕልን ማሳደግ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ዋነኛ ምሰሶ በመሆኑ እያንዳንዱ የተተከለ ችግኝ ጸድቆ ለፍሬ እንዲበቃ ሁሉም አካላት የተቀናጀ ጥረትና ክትትል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

4 days ago