Logo
Getu Temesgen
ዋናው ሰው ከወደ ኢትዮጵያ ሆነዋል
#ethiopia | ​በደቡብ አፍሪካ እና በስዋቲኒ አስተናጋጅነት በተካሄደው የ2026 የሼፎች ፌስቲቫል ላይ ኢትዮጵያ የጎላ አህጉራዊ ስኬት ማስመዝገቧ ተገለጸ።

በመድረኩ ሀገራችንን ወክለው የተሳተፉት የኢትዮጵያ ሼፎች ማህበር ፕሬዝዳንት ሼፍ ሄኖክ ዘርይሁን የምስራቅ አፍሪካ ሼፎች
ማህበር ፕሬዝዳንት በመሆን ተመርጠዋል።

የመላው አፍሪካ የምግብ አዘገጃጀት የአመጋገብ ባህልና ታሪክ በሰፊው በተዳሰሰበት እንዲሁም ዘመናዊ የሙያ ስልጠናዎች በተሰጡበት በዚህ መድረክ ላይ የተገኘው ይህ ድል ኢትዮጵያ በምግብ ቱሪዝም ዘርፍ በምስራቅ አፍሪካ ያላትን የመሪነት ሚና በጉልህ ያረጋገጠ አጋጣሚ ሆኗል።

​ይህ ታሪካዊ ስኬት ሀገራችን የታደለችበትን ልዩ እና በጣዕም የበለፀገ የምግብ ባህል፣ ሀገር በቀል ግብአቶች እንዲሁም ጥልቅ የምግብ አሰራር ጥበብ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይበልጥ ለማስተዋወቅ ሰፊ በር የከፈተ ነው።

ከዚህም ባለፈ ኢትዮጵያ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን የኢኮኖሚና የቱሪዝም ተጠቃሚነትእንደሚያሳድገው ይጠበቃል።

እንደ ቱሪዝም ሚኒስቴር ዘገባ ይህንን አንጸባራቂ ስኬት ተከትሎ ሀገራችን ቀጣዩን የ2027 የአፍሪካ ሼፎች ፌስቲቫል በክብር እንድታዘጋጅ የተመረጠች ሲሆን ዝግጅቱም በርካታ ዓለም አቀፍ የሙያው ባለሙያዎችን እና ጎብኚዎችን ወደ ሀገር ውስጥ በመሳብ የቱሪዝም እንቅስቃሴውን ለዓለም ለማሳየትና ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ከፍተኛ አቅም እንደሚፈጥር ታምኖበታል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.