1.4 ሚሊዮን የውጭ ቱሪስቶች በ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያን ጎበኙ
#ኢትዮጵያ | በ2018 በጀት ዓመት ከ1.4 ሚሊዮን በላይ የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ኢትዮጵያን መጎብኘታቸውን የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
ተቋሙ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት መድረክን ዛሬ ሲያካሂድ፣ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ መንግሥት ለቱሪዝም መሠረተ ልማት ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ ባለፉት ስምንት ዓመታት በአዲስ አበባና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎች ተገንብተው ወደ ሥራ ገብተዋል። ይህም ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪዝም መዳረሻ አድርጎ ለማስቀመጥና የሀገሪቱን ገጽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማሻሻል አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ጠቁመዋል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ1.4 ሚሊዮን በላይ የውጭ ቱሪስቶች ኢትዮጵያን የጎበኙ ሲሆን፣ ይህም ከቀደሙት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር ከ200 ሺህ እስከ 300 ሺህ የሚደርስ ጭማሪ ማሳየቱን አቶ ጌታቸው ገልጸዋል።
በተመሳሳይ ጊዜ ከ50 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን የሀገር ውስጥ ቱሪዝም መዳረሻዎችን በመጎብኘት የባህልና የማንነት እውቀታቸውን ማሳደጋቸውን የሚያሳይ ከፍተኛ መነቃቃት መታየቱንም ገልጸዋል።
በተጨማሪም አዲስ አበባን የአፍሪካ የዲፕሎማሲና የቢዝነስ ስብሰባዎች ማዕከል ለማድረግ የተያዘው ስትራቴጂ እየተሳካ በመምጣቱ፣ በዓለም አቀፍ ጉባኤዎች ላይ ወደ 166 ሺህ የሚጠጉ የውጭ እንግዶች አገልግሎት ማግኘታቸው ተገልጿል።
ነገር ግን ከአዲስ አበባ ውጭ የሆቴል ኢንዱስትሪው በፍጥነት እየተስፋፋ ቢሆንም፣ በአገልግሎት ጥራት ረገድ አሁንም ክፍተቶች እንዳሉ ተጠቁሟል። በመሆኑም የቱሪዝም ዘርፉን በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በሰለጠነ የሰው ኃይል በማጠናከር ኢትዮጵያ የበለጠ ተወዳዳሪ የቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን በትኩረት እንደሚሰራ ተገልጿል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #ethiopia #addisababa #tourisminstitute #hospitalitytraining

4 days ago