በጂቡቲ ወደብ ለ2.1 ሚሊዮን ተረጂዎች የሚውል ሰብዓዊ ዕርዳታ የመበላሸት አደጋ ተጋርጦበታል ተባለ
#ethiopia : ለ2.1 ሚሊዮን ተረጂዎች የሚውል ሰብዓዊ ዕርዳታ በጂቡቲ ወደብ የመበላሸት አደጋ እንደተጋረጠበት፣ የአፍሪካ ዴቨሎፕመንት ባንክ ግሩፕ ሪፖርት አመላከተ፡፡
በአፍሪካ ዴቨሎፕመንት ባንክ ግሩፕ (AfDB) "Country Focus Report 2025 Ethiopia" በሚል ርዕስ ከቀናት በፊት ይፋ የተደረገ ሲሆን፣ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) የሚደረጉ የውጭ ዕርዳታ ፕሮግራሞች በሰፊው እንዲቋረጥ መወሰኑን አስታውሷል።
በዚህ ውሳኔ መሠረት 2.1 ሚሊዮን ሰዎችን ለአንድ ወር መመገብ የሚያስችልና ወደ ኢትዮጵያ መግባት የነበረበት ሰብዓዊ ዕርዳታ፣ ጥቅም ላይ የመዋል ዕድል ላይኖረው ይችላል ተብሏል።
ሰብዓዊ ዕርዳታው 34,880 ሜትሪክ ቶን ማሽላ፣ ጥራጥሬና ዘይት መሆኑንና ወደ ኢትዮጵያ ለማጓጓዝ የሚከፈል ገንዘብ ባለመኖሩ ምክንያት፣ በጂቡቲ ወደብ ተይዞ እንደሚገኝ ተጠቅሷል።
Seledadotio

1 year ago