Logo
SeledaPost
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 1.4 ትሪልየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ
**

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዛሬ ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በበጀት ዓመቱ 1.4 ትሪልየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው እንደገለፁት፤ በአመቱ ከ20.1 ሚልየን በላይ መንገደኞችን እና 297 ሺህ ቶን የካርጎ ጭነቶችን ማጓጓዝ ተችሏል።

ከዚህ በተጨማሪም አየር መንገዱ የተለያዩ የአውሮፕላን ክፍሎችን የሚያመርት ሲሆን በዘንድሮው በጀት አመትም ለ68 አውሮፕላኖች የሚበቃ መለዋወጫ በማምረት ለቦይንግ ማቅረቡን ገልፀዋል።

በዚህም 6.2 ሚልየን ዶላር ገቢ ማግኘት እንደቻለ አስታውቀዋል።

Seledadotio
Seledadotio
9 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.