(ዘ-ሐበሻ ዜና ዳሰሳ) በሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን እየተካሄደ ባለው የውይይት መድረክ ላይ ተመካካሪዎች ገዥው ብልጽግና ፓርቲ ከሚያራምደው አቋም የተለዩ እና መሰረታዊ የሀገሪቱን አደረጃጀት የሚፈትኑ ወሳኝ ምክረ ሀሳቦችን እያንጸባረቁ መሆናቸው ተገለጸ። በተለይም በመንግስት አደረጃጀት፣ በክልሎች አወቃቀር፣ በአስተዳደር ሥርዓት ምርጫ እና በኮሚሽኑ አሰራር ላይ ጠንካራ ክርክሮች እና ትችቶች እየታዩ ይገኛሉ።
በ"መንግስት አደረጃጀት እና ቅርጽ" አጀንዳ ዙሪያ በተደረገው ስትራቴጂካዊ ውይይት አሁን በስራ ላይ ያለው "የብሔር ፌደራሊዝም" ያሉበትን ውስንነቶች በማረም እንዲቀጥል አብዛኛዎቹ ተመካካሪዎች ድምጽ ሰጥተዋል። ምንም እንኳን መልክዓ ምድርን መሰረት ያደረገ (ጂኦግራፊያዊ) ፌደራሊዝም እንደ አማራጭ ቢቀርብም፣ አሁን ባለው የፖለቲካ አውድ እና የብሔር ማንነት ጥያቄዎች በበዙበት ሁኔታ ሥርዓቱን ሙሉ በሙሉ መቀየር ችግሩን ሊያባብሰው ይችላል የሚል ስጋት ማየሉ ተጠቁሟል።
ይሁን እንጂ የፌደራሊዝም ሥርዓቱ ከማሻሻያ ጋር እንዲቀጥል ቢፈለግም፤ በስሩ የሚኖረው የክልሎች አደረጃጀት ግን አዲስ መልክ እንዲይዝ ጥያቄ ቀርቧል። ተመካካሪዎቹ የክልሎች አደረጃጀት ከብሔር ማዕቀፍ ወጥቶ በመልክዓ ምድራዊ አመቺነት፣ በኢኮኖሚያዊ አቅምና በሕዝብ ብዛት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ጠንካራ አቋም ማንጸባረቃቸው የውይይቱ አንዱ ትልቅ ትኩረት ሆኗል። ይህ ሀሳብ አሁን ያለውን የብሔር ፌደራሊዝም አወቃቀር ስር ነቀል በሆነ መልኩ የሚፈትን ነው።
ሌላው በምክክሩ ጎልቶ የወጣው እና ያልተጠበቀው ጉዳይ፣ ገዥው ብልጽግና ፓርቲ በሀገሪቱ "ፕሬዝዳንታዊ" የመንግስት አስተዳደር ሥርዓት እንዲተገበር አባላቱ ግፊት እንዲያደርጉ ያስተላለፈውን አቅጣጫ የሚጻረር ውሳኔ መምጣቱ ነው። በስልታዊ ቡድኖች ደረጃ የተካሄዱት ውይይቶች የገዥውን ፓርቲ ፍላጎት ወደ ጎን በማድረግ፣ አሁን ያለው "ፓርላመንታዊ" የመንግስት አስተዳደር ስርዓት እንዲቀጥል የሚለው አማራጭ ከፍተኛ ድጋፍ እንዲያገኝ አድርገዋል። ይህ ሁኔታ በምክክር መድረኩ ላይ ገዥው ፓርቲ የጠበቀው የበላይነት እየተገዳደረ መሆኑን ያሳያል።
እንዲሁም ምክክር ሂደቱን ለመምራት በኮሚሽኑ የተዘጋጁት "መሪ ጥያቄዎች" በተመካካሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ትችት አስተናግደዋል። ጥያቄዎቹ በቂ አማራጮችን ያላቀረቡ፣ ዋና ዋና ጉዳዮችን ያድበሰበሱ እና መነሳት የነበረባቸውን አንኳር ነጥቦች የዘነጉ መሆናቸው ቅሬታ አስነስቷል። አወያዮች እነዚህ ያልተካተቱ ጉዳዮች በቃለ ጉባኤ እንዲሰፍሩ ቢያደርጉም፣ ነጥቦቹ በመጨረሻው የምክረ ሀሳብ ሰነድ ላይ ስለመካተታቸው ምንም አይነት ማረጋገጫ አለመኖሩ በሂደቱ ግልጽነት እና ተአማኒነት ላይ ጥርጣሬን አሳድሯል።

9 days ago