የህዝቡን ሰቆቃ በማብዛትና በሞት አዋጅ የሚቀጥል ሕልውና የለም
******************
በትግራይ ሰማይ ስር፣ ተስፋው በጠመንጃ አፈሙዝ የተጠለፈበት፣ ህልሙ በግዴታ ጦርነት የተቀጨበት ወጣት ሰቆቃ ዛሬም ማብቂያ አላገኘም። እናት ልጇን ለትምህርት እና ለስራ ሳይሆን፣ ለማታውቀው እና ላላመነችበት የጥፋት ጦርነት እየተነጠቀች ባለችበት በዚህ አሳዛኝ ወቅት፣ የትግራይን ህዝብ ብሶት እና የወጣቱን ጩኸት ሊሰማ ያልፈለገው ህገወጥ ቡድን ዛሬም በወጣቱ እድል ላይ መቆመሩንና ነጋዴነቱን ቀጥሏል።
ዛሬ ላይ የትግራይ ወጣት ተስፋው ሲጨልምና ከስራ ፈጠራ ይልቅ ጠመንጃ ተሸከም ሲባል የቡድኑ መሪዎች ወርቅ በኮንትሮባንድ በማውጣት እና በህገወጥ ንግድ ላይ በስፋት ተጠምደዋል።
ከዚህም አልፎ ተራ ዜጎችን በማፈን፣ እንዲሁም እጅግ አሳዛኝ እና ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ የትግራይን ህጻናት ለሱዳን ወታደራዊ ግዳጅ በመሸጥ የሰው ልጅ የንግድ ልውውጥ ወንጀል እየፈጸሙ ይገኛሉ። ይህ ድርጊት የቡድኑን ዝቅታና ያለበትን ሞራል ዝቅጠት ብሎም ለህዝቡ ያለውን ንቀት በግልጽ የሚያሳይ ነው።
በወጣቱ ላይ የተቃጣው የጭካኔ አዋጅ
የወጣቱን ጩኸት ማዳመጥ የተሳነው ይህ አፋኝ ቡድን፣ ህዝቡን ከራሱ ጋር ማሰለፍ ሲያቅተው ሰሞኑን ያወጣው የሞት አዋጅ የፋሺዝም እና የጭካኔው ማሳያ ነው።
ወደ ጦርነት ካልገቡ ወጣቶችን እና ዜጎችን እስከመግደል የሚያደርሰው ይህ አዋጅ፣ እጅግ ጸረ-ህዝብ እና ህገ-መንግስታዊነትን የጣሰ ነው። በዚህ በሰለጠነ ዘመን በየትኛውም የዓለም ክፍል ሊታሰብ የማይችል ይህ ጭካኔ የተሞላበት ህግ፣ ቡድኑ በህዝብ ላይ የተጫነ መቅሰፍት እንጂ የህዝብ ወገን አለመሆኑን ያረጋግጣል። የትግራይ ወጣት ህይወት ለቡድኑ መሪዎች የስልጣን እድሜ ማራዘሚያ ርካሽ ማገዶ ሆኖ ቀጥሏል።
ወጣቱ በግድያ እና በእስራት እየማቀቀ ባለበት በዚህ ሰዓት፣ የቡድኑ መሪዎች በሚስጥራዊ ስብሰባዎቻቸው ላይ የውጭ ኃይሎች ተሸክመው አዲስ አበባ እንደሚያስገቧቸው እና ስልጣን ላይ እንደሚያወጧቸው ሲያልሙ ይሰማሉ።
ይህ ከህዝብ የተነጠለ፣ የራሱ አቅም የሌለው እና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለውጭ ኃይሎች አሳልፎ ለመስጠት የተዘጋጀ ርካሽ ስብስብ፣ የትግራይን ወጣት ሰቆቃ ሊሰማ ቀርቶ ሊረዳውም የሚችል የሞራል ልዕልና የለውም።
የቡድኑን ጸረ-ህዝብ አዋጅ እና የግድያ ዛቻ በመሸሽ፣ በርካታ የትግራይ ወጣቶች ስርዓቱን እያወገዙ ወደተለያዩ አካባቢዎች ለማምለጥ እየሞከሩ ነው። ይህ እርምጃ የወጣቱ እውነተኛ ጩኸት እና የተቃውሞ ድምጽ ነው። ከስርዓቱ ያመለጡ ወጣቶች የሚያስተላልፉት የእውነት ቃል፣ የትግራይ ህዝብ በቡድኑ ላይ ያለውን ምሬት እና የለውጥ ፍላጎት የሚያንጸባርቅ ነው።
በአጠቃላይ፣ የትግራይ ወጣት ከዚህ አቅመ-ቢስ፣ ተላላኪ እና ጨካኝ የሽፍታ ስብስብ ነጻ ወጥቶ ከታላቋ ኢትዮጵያ የልማት እና የሰላም ጉዞ ጋር መቆራኘት ይፈልጋል።
ዛሬም ኢትዮጵያ እንደትናንቱ የውስጥ ባንዳዎችን እና የውጭ ሴረኞችን እኩይ ምኞት እያከሸፈች፣ በልማት ሉዓላዊነቷን ታረጋግጣለች።
የትግራይም ወጣት የዚህ ትልቅ ሀገራዊ ጉዞ ማዕቀፍ አካል በመሆን የሰላም እና የብልጽግናው ተጠቃሚ የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። የደም ነጋዴው እና ጩኸት አላዳምጥ ያለው ህገወጥ ቡድንም ይህ በህዝብ የመነገድ መንገዱ ማብቂያው ጊዜ ሩቅ አይደለም።
በመሀመድ ፊጣሞ

9 days ago