የምክክር ኮሚሽኑ የአራት ዓመታት ጉዞ እና የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው አዲስ ምዕራፍ
*********************
ኢትዮጵያ ለዘመናት የዘለቁ ውስብስብ ሀገራዊ ልዩነቶችንና ቅሬታዎችን በሰለጠነ መንገድ፣ በውይይትና በምክክር ለመፍታት ያደረገችው ጥረት ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ባለፉት አራት ዓመታት በርካታ ፈታኝና መሠረታዊ የዝግጅት ሥራዎችን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ደግሞ የጠቅላላው ሂደት ማጠቃለያ ወደሆነው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ተሸጋግሯል።
ኮሚሽኑ የተጣለበትን ታሪካዊ ኃላፊነት ለመወጣት ባለፉት ዓመታት ትኩረት ሰጥቶ የሠራቸው ዐበይት ተግባራት በሚከተሉት ዋና ዋና ዘርፎች የሚከፈሉ ናቸው።
✅ የተቋም ግንባታና የህግ ማዕቀፍ ዝግጅት
ኮሚሽኑ ሥራውን በግልጽነትና በተጠያቂነት መምራት የሚያስችሉ መመሪያዎችን፣ የሥነ-ምግባር ደንቦችንና የአሠራር ሥርዓቶችን ዘርግቷል። ነፃነቱንና ገለልተኝነቱን በጠበቀ መልኩ የተዋቀረው ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን፣ የኅብረተሰቡን እምነት ለመገንባት የሚያስችሉ በርካታ የማንቃትና የማስተዋወቅ ሥራዎችን አከናውኗል።
✅ የባለድርሻ አካላት እና የቁልፍ ተሳታፊዎች ልየታ
የምክክር ሂደቱ ሁሉንም አሳታፊ (Inclusive) ለማድረግ በሁሉም የሀገራችን ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች እስከ ወረዳና ቀበሌ ድረስ የወረዱ የባለድርሻ አካላት ልየታዎች ተካሂደዋል።
በሂደቱም የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የእድሜ ባለጸጎች፣ አካል ጉዳተኞች፣ ነጋዴዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ማህበራት፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች፣ የመንግሥት አካላትና የጸጥታ ተቋማት ተወካዮች እንዲሳተፉ ተደርጓል።
✅ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት
የምክክር ሂደቱ እውነተኛ የሕዝብ ድምፅ እንዲሆን በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች ደረጃ ሰፊ የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረኮች ተካሂደዋል።
በእነዚህ መድረኮች ኅብረተሰቡ ለሀገራዊ አንድነት፣ ለሰላም፣ ለፍትህና ለሕገ-መንግሥታዊ ጉዳዮች መፍትሔ ይሆናሉ ያላቸውን ሐሳቦችና ቅሬታዎች በነፃነት እንዲያቀርብ ተደርጓል።
✅ የአጀንዳዎች ውህደትና ማዋቀር
ከመላው የሀገራችን አካባቢዎች የተሰበሰቡ የተለያዩ አጀንዳዎች በባለሙያዎችና በኮሚሽነሮች አማካኝነት በጥራት ተደራጅተው፣ ተመሳሳይነታቸው ተለይቶ እና ተዋቅረው ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤው እንዲቀርቡ ተደርገዋል።
✅ አሁን ላይ ያለው የሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ምዕራፍ
ባለፉት አራት ዓመታት የተሠሩት መሠረታዊ ሥራዎች ውጤት የሆነው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፣ አሁን ላይ ትልቁ የትኩረት ማዕከል ሆኗል። ይህ ጉባኤ ከየአካባቢው የተወከሉ ከ4 ሺህ በላይ ተመካካሪዎች እና ቁልፍ ባለድርሻ አካላት በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በስፋት የሚመክሩበት ታሪካዊ መድረክ ነው።
✅ የጉባኤው ዋና ዋና ትኩረቶችና ግቦች
1.በአጀንዳዎች ላይ በጥልቀት መምከር፡- ከመነሻው ጀምሮ ከተሰበሰቡት አጀንዳዎች መካከል ዋና ዋና ሀገራዊ መግባባት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ለአብነት ያህል ሕገ-መንግሥታዊ ማሻሻያዎች፣ የሀገረ-መንግሥት ግንባታ፣ የታሪክ ትርክት፣ የሰላምና ደኅንነት ሥርዓት ላይ ነፃና ግልጽ ውይይት ማድረግ።
2. የተሰበሰቡ ሐሳቦችን ማደራጀትና ማቀራረብ፡- ኮሚሽኑ ከታች ጀምሮ ያሰባሰባቸውን አጀንዳዎች ላ በጥልቀት በመምከር በሀገራዊ ፍላጎቶችና የጋራ እሴቶች ላይ ያተኮረ መግባባት መፍጠር።
3. የመፍትሔ ሐሳቦችና የውሳኔ አስተያየቶች ማዘጋጀት፡- በምክክር ጉባኤው በሚደረጉ ውይይቶች መሠረት ለሀገራዊ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ የሚሆኑ የፖሊሲ፣ የሕግና የተቋማት ማሻሻያ ሐሳቦችን አዘጋጅቶ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትና ለሕዝብ ማቅረብ ናቸው።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባለፉት አራት ዓመታት የተጓዘበት መንገድ በፈተናዎች እና በተስፋዎች የተሞላ ቢሆንም፣ በሀገራችን በረጅም ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው በሆነው በዚህ አሳታፊ ሂደት፣ ከቀበሌ እስከ ሀገር አቀፍ ደረጃ የተካሄዱት እንቅስቃሴዎች የሕዝብን ድምፅ የመስማት ትልቅ መሠረት ጥለዋል።
አሁን ላይ እየተካሄደ ያለው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ደግሞ፣ የዚሁ ሁሉ ድካም ፍሬ የሚታይበት፣ የኢትዮጵያን የወደፊት የፖለቲካና የማኅበራዊ መስመር የሚቀርጽ በመሆኑ የሁሉም ዜጎች፣ የፖለቲካ ኃይሎች እና ባለድርሻ አካላት በጎ ፈቃድና ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ ነው።
በአድማሱ አራጋው
#ethiopianbroadcastingcorporation #nationaldialogue #ethiopiannationaldialogue #inclusivedialogue

10 days ago