ስብራቱ የተጠገነው የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ዓመታት የትምህርት ዘርፉን ጥራት እና ተደራሽነት ችግሮች ለመቅረፍ በተከናወኑ ተግባራት ዘርፈ ብዙ ስኬቶች ተመዝግበዋል፡፡
የትምህርት ጥራት ለሀገር ሁለንተናዊ እድገት በእውቀት እና በአዕምሮ የዳበረ የሰው ሃይል ለመፍጠር፣ ለኢኮኖሚ እድገት እና ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡
በሀገራችን ለበርካታ ዓመታት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ ቢሆንም የተደረጉ ጥረቶች በሚፈለገው ልክ ውጤት አላመጡም፡፡
በዚህም ባለፉት ዓመታት በትምህርት ዘርፉ በተስተዋሉ ችግሮች ሳቢያ በእውቀትና በክህሎት የዳበረ የሰው ሀይል በማፍራት ረገድ ክፍተቶች ሲስተዋሉ ነበር፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በአንድ ወቅት÷ በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት ችግር ውስጥ ነጠላ ምክንያቶች የሉም፤ ችግሮቹ ዘርፈ ብዙ በመሆናቸው ሁለንተናዊ መፍትሄ ይሻሉ ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ዓለማየሁ ተ/ማሪያም (ፕ/ር) በበኩላቸው÷ትምህርት ሲባል ክፍል ቆጥሮ መጨረስ ወይም ዲግሪ መጫን ሳይሆን ጥራት ያለውን የትምህርት ሥርዓት ዘርግቶ ተግባራዊ ማድረግና የሥነ ምግባር እና የእውቀት ለውጥ ማምጣት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የችግሩን ግዝፈት የተረዳው የመደመር መንግሥት በዘርፉ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ በትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት ዙሪያ በርካታ የማሻሻያ ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡
ለአብነትም ተማሪዎች ከመሰረታቸው ጀምሮ የዳበረ ክህሎት እንዲኖራቸው ለማድረግ መንግሥት ደረጃቸውን የጠበቁ የቅድመ መደበኛ እና መደበኛ ትምህርት ቤቶች ግንባታን እያስፋፋ ይገኛል፡፡
ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች ልጆቻቸው ከትምህርት ገበታ እንዳይቀሩ ለማድረግ የተጀመረው የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት አካል ነው፡፡
የትምህርት ኢንቨስትመንትን የማስፋፋት፣ ሥርዓተ ትምህርቱን የማሻሻል፣የመምህራንን አቅምና ብቃት የማሳደግ ሥራዎች በትኩረት እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካዳሚያዊ ነጻነታቸው ተጠብቆ እንዲሠሩ፣ በአስተዳደር እና በሰው ኃይል ልማታቸው የተሻሉ እንዲሆኑ መንግሥት በርካታ ድጋፎችን አድርጓል፡፡
በተመሳሳይ የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ኢኮኖሚው የሚፈልጋቸውን፣ እጃቸው የሰላ፣ የተግባቦት አቅማቸው የዳበረ እና ምርታማነትን የሚያረጋግጡ ባለሙያዎችን እንዲያፈሩ ለማደረግ መንግሥት የሚያደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በዚህም ከኩረጃ ነጻ የሆነ፣በራሱ የሚተማመን፣ ለችግሮች መፍትሔ መስጠት የሚችል ትውልድ ከማፍራት በተጨማሪ ጥራት ያለው ትምህርት ተደራሽ ማድረግ ተችሏል፡፡
በሚኪያስ አየለ

10 days ago