ከ700 በላይ የዓለም መሪዎችንና ፈጣሪዎችን የሚያሰባስበው ጉባኤ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው!
#fastmereja :- ታሪካዊው «የዓለም አቀፍ የሕዝቦች ጉባኤ አፍሪካ» (World Public Summit Africa) ከሐምሌ 22 እስከ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. በዲፕሎማሲያዊቷ መዲና አዲስ አበባ በደመቀ ሁኔታ እንደሚካሄድ በዛሬዉ እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ።
«አዲስ ዓለም አፍሪካ የጋራ መፃኢ እድልን በመቅረጽ ረገድ» በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ ከ700 በላይ የመንግሥት መሪዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ የቢዝነስ ባለሀብቶች፣ የፈጠራ አውጪዎች፣ ምሁራን፣ የሲቪል ማህበራት ተወካዮች፣ የብዙሃን መገናኛ ባለሙያዎች እና የባህል መሪዎች ከመላው አፍሪካና ከሌሎች የዓለም ክፍሎች ይሳተፋሉ።
ጉባኤው በስፖርት አማካኝነት በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ከሚያቀራርበው የዓለም ዋንጫ ጋር በሚመሳሰል መልኩ፡ የተለያዩ ዓለም አቀፍ አካላትን በማሰባሰብ በጋራ ሀሳብ የመለዋወጥ፣ ጠንካራ አጋርነቶችን የመፍጠር እና ለዓለማችን መሠረታዊ ኢኮኖሚያዊ፣ ቴክኖሎጂያዊ፣ ማህበራዊ እና የልማት ጉዳዮች መፍትሔ የመፈለግ ዓላማን ማሰናዳቱን ተገልጿል።
ይህ ታላቅ መድረክ በአፍሪካ አህጉር ሲካሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን፣ ይህም አፍሪካ በዓለም አቀፍ የንግድ፣የፈጠራ፣ የዘላቂ ልማት፣ የሕዝብ ዲፕሎማሲ እና የሁለገብ ትብብር ውይይቶች ላይ ያላትን እየጎለበተ የመጣ ማዕከላዊ ሚና የሚያንፀባርቅ እንደሆነ በመግለጫው ወቅት ተመላክቷል።
የጉባኤው ዋና ማዕከል ከሆኑት ዝግጅቶች አንዱ «አንድነት» (Unity) የተሰኘው ዓለም አቀፍ ዘመናዊ የኪነ-ጥበብ ኤግዚቢሽን መሆኑን አዘጋጆቹ ጠቁመዋል።
ኤግዚቢሽኑ ከ16 የአፍሪካ ሀገራት (ኢትዮጵያ፣ ካሜሩን፣ ኮንጎ ዲ/ሪ፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ማዳጋስካር፣ ናሚቢያ፣ ናይጄሪያ፣ ሩዋንዳ፣ ሴኔጋል፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሱዳን፣ ታንዛኒያ፣ ቱኒዚያ፣ ዛምቢያ እና ዚምባብዌ) የተጣጣሙ ታዋቂ አርቲስቶችን እንዲሁም የአፍሪካና የዳያስፖራውን ታሪካዊ ቁርኝት የሚያሳይ አፍሮ-ብራዚላዊ አርቲስትን ያሰባስባል።
በተጨማሪም «የዛምቤዚ ወንዝ፡ ኢኮኖሚ፣ ማህበረሰብ እና መንፈስ» በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሳይንሳዊ ጥናት የሚቀርብ ሲሆን፣ ጥናቱ ወንዙ በስድስት የአፍሪካ ሀገራት (አንጎላ፣ ዚምባብዌ፣ ዛምቢያ፣ ናሚቢያ፣ ቦትስዋና እና ሞዛምቢክ) እድገት ላይ ያለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ በስፋት እንደሚመረምር ነዉ የተገለፀዉ።
የጠቅላላው ምክር ቤት ሊቀመንበር አማካሪ ያኒና ዱቤይኮቭስካያ እንደገለፁት «አንድነት ማለት ወጥ መሆን ማለት አይደለም፤ ይልቁንም ለባህል ብዝሃነት ከሚሰጥ አክብሮት፣ ከእርስ በእርስ እምነት፣ ክፍትነት እና ለመደማመጥ ከሚኖር ፈቃደኝነት የሚወለድ መሆኑን ገልፀዉ ስለዚህም ጥበብ ልክ እንደ ስፖርት ሁሉ የሰው ልጅ የጋራ ቋንቋ እና የሕዝብ ዲፕሎማሲ መሣሪያ ነው። ቃላት ብቻቸውን ማሳካት በማይችሉበት ቦታ ሰዎችን ያቀራርባል።» ብለዋል።
የሰርቭ ግሎባል (Serve Global) ምክትል የሀገርውስጥ ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ነጋሽ እንደገለፁት«ጉባኤው በንግድ ድርድር ላይ ሳይሆን አልሞ የተነሳና የእውነተኛ አንድነትን በማሳየት ለሁሉም የዓለም ሕዝቦች የሚሰራ አዲስ ዓለም ለመገንባት መንገድ ይጠርጋል።» ሲሉ ገልጸዋል።
ይህ በአዲስ አበባ የሚካሄደው የአፍሪካ ጉባኤ ዓመቱን ሙሉ የሚቀጥል ዓለም አቀፍ የትብብር መድረክ አካል ሲሆን፣ ቀጣዩ ዓለም አቀፍ መድረክ በመስከረም ወር በሩሲያ ሞስኮ እንደሚካሄድ ያኒና ዱቤይኮቭስካያ እና ታሪኩ ነጋሽ ጨምረው አስታውቀዋል።

11 days ago