የኢትዮጵያን የሪል እስቴት ገበያ ለአለም አቀፍ ኢንቨስተሮች የሚያስተዋውቅ አዲስ ስምምነት ተፈረመ!
#fastmereja I የኢትዮጵያ ሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር (EREDA) እና ዶክሳ ቢዝነስ ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማ. በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ዘርፍን በሀገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ለማጠናከር የሚያስችሉ ሁለት ስትራቴጂካዊ የመግባቢያ ሰነዶችን በዛሬዉ እለት ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱ የሪል እስቴት ዘርፉን ትብብር ለማሳደግ፣ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ኢንቨስትመንት እድሎችን ለማስፋፋት እንዲሁም የዲያስፖራውን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተገልጻል፡፡
በስምምነቱ መሠረት በሀገር ውስጥ የኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበርን ተቋማዊ አቅም ማጠናከር፣ የአባልነት መስፋፋትን መደገፍ፣ በመንግስት እና በግል ዘርፍ መካከል ያለውን ትብብር ማሳደግ እና የዕውቀት ልውውጥ መድረኮችን በጋራ ማዘጋጀት ዋና ዋና ትኩረቶች ሲሆኑ በዚህም ዶክሳ ቢዝነስ ትሬዲንግ ለተመረጡ መርሃግብሮች የኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር (EREDA) ተመራጭ የኢቨንት አስተባባሪ አጋር ሆኖ እንደሚሰራም ነዉ የተገለፀዉ።
በሌላ በኩል ስምምነቱ የዲያስፖራ ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት እና የውጭ ምንዛሬ ገቢን ለማሳደግ ያለመ ሲሆን፣ የመጀመሪያዎቹ አለም አቀፍ የሪል እስቴትና ኢንቨስትመንት ትስስር ፕሮግራሞች በሪያድ (ሳውዲ አረቢያ)፣ በጆሃንስበርግ (ደቡብ አፍሪካ) እና በእስራኤል እንደሚካሄዱ ተጠቅሷል፡፡
ሁለቱ ተቋማት ቀደም ሲል እንደ "Addis Africa Real Estate Expo 2026" ያሉ ትልልቅ መድረኮችን በጋራ ማዘጋጀታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በቀጣይም የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች በግልጽነት እና በተጠያቂነት መመሪያዎች የሚመሩ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ዶክሳ ቢዝነስ ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማ. በቢዝነስ ልማት፣ በስትራቴጂካዊ ግንኙነት፣ በኢቨንት ማስተባበር፣ በማርኬቲንግ ኮሙኒኬሽን እና በባለድርሻ አካላት ትስስር ላይ የተሰማራ ድርጅት ሲሆን፣ ቢዝነሶችን፣ ባለሀብቶችን፣ መንግስታዊ ተቋማትን እና ማህበረሰቡን የሚያገናኙ ዘላቂና ፈጠራ ያላቸው መድረኮችን በመፍጠር ለኢኮኖሚያዊና ለኢንዱስትሪ ልማት አስተዋፅኦ ያደርጋል::

3 months ago