(ዘ-ሐበሻ ዜና) የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋፍ ሳላም የሀገሪቱ ሰራዊት አዲስ በተሰማራበት ደቡባዊ የሊባኖስ መንደር ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፣ እስራኤል ከተቆጣጠረቻቸው የደቡብ ሊባኖስ ግዛቶች ሙሉ በሙሉ እንድትወጣ ለማድረግ የፖለቲካ እና የዲፕሎማሲ ጥረታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት የሊባኖሱ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን በኋይት ሀውስ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ተገናኝተው የእስራኤል ጦር ከሊባኖስ ግዛት በአስቸኳይ እንዲወጣ ጥሪ ባቀረቡ ማግስት የተደረገ ነው።
በአሜሪካ አሸማጋይነት ባለፈው ወር በተደረሰው ስምምነት መሠረት የሊባኖስ ሰራዊት በደቡባዊ ክፍሎች እየተሰማራ የሄዝቦላህን ትጥቅ እንዲያስፈታ እና የእስራኤል ጦር ደግሞ ደረጃ በደረጃ ከቀጠናው እንዲወጣ የታቀደ ቢሆንም፣ ሄዝቦላህ ስምምነቱን ባለመቀበል ትጥቅ ላለመፍታት አቋም ይዟል።
በሌላ በኩል የእስራኤል ጦር በደቡብ ሊባኖስ በሚገኘው የታሪካዊው ዱቢዬ ቤተ-መንግሥት ላይ ባንዲራዋን መስቀሏን ተከትሎ የሊባኖስ መንግሥት ድርጊቱን ትንኮሳ ሲል የኮነነ ሲሆን፣ የሀገሪቱን የሉዓላዊነት መብት ለማስከበር እንደሚሰራ ገልጿል።

15 days ago