(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ ኮንግረስ ለሱዳን በተዘጋጁ 2 ረቂቅ ህጎች ላይ ውይይት ማድረግ ጀመረ፡፡ በሱዳን የሚካሄደው ጦርነት በአሜሪካ ኮንግረስ ወደአዲስ ምእራፍ መሸጋገሩን አልአይን ዘግቧል፡፡ እንደዘገባው ‹‹በሱዳን ሰላም ማምጣት ይችላሉ›› የተባሉ ሁለት ህጎችን ለማውጣት የአሜሪካ ኮንግረስ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን አንደኛው በተወካዮች ምክር ቤት ሌላኛው በሴኔት የሚፀድቁ ናቸው፡፡
በረቂቅ ህጎቹ ላይ የሪፐብሊካንመ ሆነ የዲሞክራት አባላት ይሁንታ እየሰጡ መሆናቸውንም አስረድቷል፡፡ ከአሜሪካ ኮንግረስ ድረገፅ ላይ እንዳገኘው በጠቀሰው መረጃ የተወካዮች ምክር ቤት ‹‹ሱዳኒስ ፒስ አክት›› የተሰኘ ህግን ለማፅደቅ እየተነጋገረ ሲሆን ይህ ህግ ዋነኛ አላማው አጠቃላይ ማእቀብ፣ ሰላማዊ ሰዎችን መጠበቅ፣ የሰብአዊ እርዳታ ተደራሽነትና የፖለቲካ ሂደት ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጿል፡፡
የአሜሪካ ሴኔት ደግሞ ‹‹ሱዳን ኤክስተርናል አግሬሽን ኤንድ ኮንፍሊክት ኢስካሌሽን ፕሪቬንሽን አክት 2026›› የሚል መጠሪያ ያለው መሆኑን ያስታወቀው ዘገባው ይህኛው በሱዳን ጦርነት ድርሻ ያላቸውን የውጭ አገር ድርጅቶችና ግለሰቦች የማእቀብ ሰለባ እንደሚያደርግ አስረድቷል፡፡

16 days ago