Logo
SeledaPost
ኤሌክትሮኒክስ ላይ ረጅም ሰዓት የሚያሳልፉ  የልዩ ፍላጎት  ልጆች የንግግር እና የመግባባት ክህሎታቸውን ሊጎዳ እንደሚችል ተነገረ
 
ልዩ ፍላጎት የሚያስፈልጋቸው ታዳጊዎች በቤት ውስጥ ረጅም ጊዜን በሚያሳልፋበት የክረምት ወቅት ላይ ቴሌቭዥንን ጨምሮ ከሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ነገሮች መራቅ ይኖርባቸዋል። ልዩ ፍላጎት ያላቸው ልጆች ለአእምሮ እድገታቸው  እንቅስቃሴ ያሏቸው ጨዋታዎችን እንዲጫወቱ ፣ በአእምሮ የሚሰሩና የሚገጣጠሙ  መጫዎቻዎች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ማገዝ  ያስፈልጋል ሲሉ የፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ብሔራዊ ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ  ወ/ሮ ሸዋጌጥ ክብረት  ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ  ገልጸዋል።
 
ልዩ ፍላጎት  ያላቸው ታዳጊዎች  ትምህርት ቤት ስለሄዱ ብቻ ውጤታማ መሆን ስለማይችሉ ብቻቸውን ከማዋል ይልቅ ልጆች ያሉባቸው እንዲሁም ሊደሰቱባቸው የሚችሉባቸው ቦታዎች ላይ እንዲሆኑ ማድረግ የመግባባት ክህሎታቸውን ለማዳበር ያግዛል። ከቴሌቪዥን እና ከሞባይል ጋር ረጅም ሰዓትን የሚያጠፉ የልዩ ፍላጎት ልጆች ከንግግር እና ከመግባባት ችሎታ ወደ ኋላ እንዲቀሩ ያደርጋቸዋል።
 
ይህ አይነቱ ችግር ያለባቸው ልጆች  ንዴታቸውን የሚገልጹት ራሳቸውን በመጉዳት ሊሆን ስለሚችል ከልጅነት ጀምሮ በሚኖራቸው አስተዳደግ  ላይ ከፍተኛ  ትኩረት ማድረግ እና ሊያናድዳቸዉ የሚችሉ ነገሮችን መቅረፍ  ያስፈልጋል።ዋና ስራ አስኪያጇ አክለውም ወላጆች ይህን ህመም የማመን ችግር እንደሚገጥማቸው ገልፀው፤ ስልጠና በመውሰድ  ለዚህ ጉዳይ መፍትሄ ማግኘት እንደሚችሉ  ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
 
Seledadotio
Seledadotio
15 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.