የምክክር ጉባኤው የነገዋ ኢትዮጵያ በምን ዓይነት መሠረት ላይ መገንባት እንዳለባት ሁላችንም ቆም ብለን እንድናስብ አድርጎናል - ኡስታዝ አህመዲን ጀበል
******************
አሁን በሂደት ላይ ያለው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በሀገራችን ለዘመናት ሳይፈቱ የቆዩ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ልዩነቶችን ለመፍታት ትልቅ ዕድል መፍጠሩን የጉባኤው ተሳታፊ የሆኑት ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ገለጹ።
ኡስታዝ አህመዲን ስለጉባኤው ሂደት በሰጡት አስተያየት፣ ምክክሩ ሁሉንም ችግሮቻችንን በአንዴ ሊያራግፍልን ባይችል እንኳ፣ አጀንዳ ያለው ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በመድረኩ በመገኘት በዋና ዋና ሀገራዊ ችግሮቻችን ላይ ተወያይቶ የመፍትሔው አካል መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።
የምክክር ጉባኤው በተለይ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ፣ የብሔር ብሔረሰቦች እና በአጠቃላይ የዜጎች የውክልና ጥያቄዎች የሚመለሱበትን እና የሕዝቦች አብሮነት የሚጠናከርበትን ማዕቀፍ ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።
እንደ ኡስታዝ አህመዲን ገለጻ፣ በምክክር ጉባኤው እስከ አሁን የተካሄዱት ውይይቶች ሁለት ዋና ዋና አዎንታዊ ፋይዳዎችን አስገኝተዋል፦
አንደኛ፣ ከተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የተወከሉ ተሳታፊዎች ያሏቸውን ቅሬታዎች በመጋራት እርስ በርስ እንዲተዋወቁና አንዱ የሌላውን ብሶት እንዲረዳ ጉባኤው ሰፊ በር ከፍቷል።
በዚህም፣ ቀደም ሲል በየአካባቢው ታፍነው የቆዩ ቅሬታዎች ይፋ በመውጣታቸው የጋራ ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል።
ሁለተኛ፣ ለረጅም ጊዜ ሳይፈቱ የቆዩ አከራካሪ የሆኑ ጉዳዮችም ጠረጴዛ ላይ ቀርበው ውይይት እንዲደረግባቸው አስችሏል።
ውይይቱ ሙሉ መፍትሔ ባያመጣ እንኳ፣ በልዩነቶቹ ዙሪያ መነጋገር መቻሉ በራሱ የመግባባት መንፈስ ይፈጥራል ብለዋል።
በተጨማሪም የምክክር ሂደቱ የነገዋ ኢትዮጵያ በምን ዓይነት መሠረት ላይ መገንባት እንዳለባት ሁሉም ወገን ቆም ብሎ እንዲያስብ መንገድ የከፈተ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በአጠቃላይ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ሁሉንም ወገኖች የመፍትሔ አካል በማድረግ ኢትዮጵያዊ አብሮነትን ለማጠናከር በሚያስችል ተስፋ ሰጪ ሂደት ላይ መሆኑን ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ገልጸዋል።
በመሐመድ ፊጣሞ
#ethiopia #nationaldialogue #nationalconsensus #ebc

3 months ago