ከአየር ንብረት ጥበቃ እስከ ዘርፈ ብዙ የማህበረሰባዊ ኑሮ መሻሻል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የኢትዮያን የደን ሽፋን በከፍተኛ መጠን እንዲጨምር አስችሏል፡፡ በዚህም የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳቱን ለመቀነስና ብሎም ለመቆጣጠር ከማስቻሉ ባለፈ ለምግብነት የሚውሉ የተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞች በመትከል የአርሶ አደሩ ገቢ እንዲያድግ ሚናው ከፍተኛ ነው፡፡
የደን ሽፋን መጨመር አርሶ አደሩ ለሚያካሂደው የንብ ማነብ ተግባር ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ በማር ምርት ከአፍሪካ መሪ ስትሆን በዓለም ደረጃ ደግሞ ካ አስር ሀገራት አንዷ መሆኗን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሀገራችንን የማር ምርት በብዛትም በጥራትም እንዲጨምርና ከዘርፉ እንድትጠቀም ያግዛል፡፡
በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከሚተከሉ ችግኞች ውስጥ የእንስሳት መኖ ከፍኛውን ድርሻ ይወስዳል፡፡ ይህ ደግሞ በእስሳት እርባታ ረገድ ምርትና ምርታማነትን እንዲጨምር ቀጥተኛ ሚና እየተጫወተ ነው፡፡ ለእንስሳት በቂ የመኖ አቅርቦት ስለሚኖር የሚሰጡት የወተት እና ስጋ ምርቶች መጠንና ጥራት እንዲጨምር ዓይነተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡ በዚህም የአርብቶ አደሩን እና የአርሶ አደሩን ገቢ እንዲያድግ እያገዘ ነው፡፡
የአርሶ አደሩን እና አርብቶ አደሩን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ አልፎ ምርቱን ለገበያ ማቅረብ የሚችልበትን እድል ከፍቷል፡፡ አርሶ አደሩ የአፈርን ለምነት አስጠብቆ ማቆየት መቻሉ የሚዘሩት የሰብል ምርቶች የበለጠ ምርታማ እንዲሆኑም ያግዛል፡፡
በየአካባቢው በችግኝ ማፍላት እንዲሁም በመንከባከብ ሂደት ተደራጅተው መስራት እንዲችሉ የስራ ዕድል በመፍጠር ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ማስተዳደር እንዲችሉ በር የከፈተ ነው፡፡
ለምግብነት የሚውሉ ምርቶች በተጨማሪ፣ ለመድኃኒትነትና ለተለያዩ ተግባራት የሚስፈልጉ ግብዓቶችን ማግኘት በማስቻሉ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመቀነስ በራስ ምርት የመጠቀም አቅምን እና ልምድን ያሳድጋል ፡፡
በአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ከተተከሉ የችግኝ ዓይነቶች ውስጥ አካባቢን ለማስዋብ የሚያገለግሉ ዕፅዋትም ይገኙበታል፡፡ ዕፅዋቱ የአካባቢ ውበትን ከመጨመር ባሻገር ለዜጎች ሳቢ፣ ጤናማና ነፋሻ ከባቢን ይፈጥራል፡፡
ኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርን ከአየር ንብረት ለውጥ መግቻነት ባለፈ አረንጓዴ ዲፕሎማሲ እያካሄደችበት ትገኛለች፡፡ የአየር ንብረት ለውጥን ለመታገልና ለማስቆም ከውጭ እርዳታ ከመጠበቅ ይልቅ በራስ አቅም ተግባራዊ መፍተሄ መስራትን በአብነት ያሳየችበትና የዓለምን ቀልብ የሳበችበት ሥራ ሆኗል፡፡
ይህ ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት እንድታገኝ በማድረግ የዲፕሎማሲ አቅሟን አሳይቷል፡፡ ይህ በተግባር የታዬ ጥረቷ ባለፈው መስከረም ወር ሁለተኛውን የአፍሪካ አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ማዘጋጀቷ እና የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን (ኮፕ32) ለማዘጋጀት እንድትመረጥም አስችሏታል፡፡
በአረንጓዴ አሻራ ዙሪያ ማህበረሰቡ ያለውን መረዳት አሳድጓል፣ ያልተከሉት አይበቅልምና ለትውልድ መትከል የሚገባውን ነገር በሚገባ ተገንዝቧል፡፡
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በመንግስትና በማህበረሰቡ ትብብር የሚተገበር እና ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ቀጥሎ ሁለተኛው ታላቅ የህዝብ ንቅናቄ የታየበት ብሔራዊ ፕሮጀክት ነው፡፡
ኢትዮጵያ ለነገ ትውልድ የሚሻገር ጥሪት፣ የራስን ችግር በራስ አቅም የመፍታት ልምድን እንዲሁም ኢኮኖሚዋ የጠነከረ ሀገርን ለትውልዱ እየተከለች ትገኛለች፡፡
በቤተልሔም ግርማ

17 days ago