Logo
YenetaTube
ትራንስፎርመር ሲሰርቅ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

በባህር ዳር ሪጅን በአዊ ዞን እንጅባራ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ስር በሚገኘው እንጅባራ ከተማ 02 ቀበሌ ልዩ ቦታው "ዘር ማበጠሪያ ሰፈር" በተባለ አካባቢ፣ ለማህበረሰቡ አገልግሎት የሚሰጥ ባለ 200 ኪ.ቮ.አ) ትራንስፎርመር በመዝረፍ ላይ የነበረ ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተያዘ።

ድርጊቱ የተፈጸመው ትናንት ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት ላይ አካባቢውን ሆን ብሎ ከኤሌክትሪክ ኃይል ውጭ በማድረግ መሆኑ ታውቋል።

ይህ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ስርቆት ሲፈፅም የተገኘ ግለሰብ የተያዘው በአካባቢው ማህበረሰብና በጸጥታ ሃይሉ በተደረገ የተቀናጀና ንቁ ክትትል ሲሆን፣ ተጠርጣሪው ግለሰብ የፈታቸውን የትራንስፎርመር ማቴሪያል ጨምሮ በአካባቢው ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል።

በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬና በህዝብ ሃብት የሚገነቡ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ የሚፈጸሙ መሰል ስርቆቶች ለሃይል መቆራረጥ ዋነኛ መንስኤ እየሆኑ ነው። ድርጊቱ በሃገር፣ በተቋምና በማህበረሰብ ላይ እያደረሰ ያለው ዘርፈ-ብዙ ጉዳት ከቀን ወደ ቀን እየከፋ መምጣቱም ተገልጿል።

በመሆኑም በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን መከላከልና መጠበቅ የሁሉም ዜጋ ሃላፊነት በመሆኑ፣ በየደረጃው የሚገኘው የህብረተሰብ ክፍል እነዚህን ውድ የልማት አውታሮች እንደ ራሱ ንብረት አድርጎ በንቃት ሊጠብቃቸውና ሊከላከልላቸው እንደሚገባ ተቋሙ ጥሪ ያቀርባል።
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

17 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.