የኢትዮጵያውያን የሽምግልና ሥርዓት፤ የይቅርታና የእርቅ ጥበብ ማኅደር
***********************
የሽምግልና ሥርዓት ኢትዮጵያውያን ከሚኮሩባቸውና በማኅበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ክብር ከሚሰጣቸው መልካም አገራዊ እሴቶች መካከል አንዱ ነው፡፡
ይህም የሽምግልና ሥነ ሥርዓት በመከባበር እና በመተሳሰብ ላይ የተመሰረተው የሽምግልና ሥርዓት፥ በማኅበረሰቡ ውስጥ የሚፈጠሩ ውስብስብ አለመግባባቶችን ሳይቀር በይቅርታ እና በእርቅ እንዲፈቱ በማድረግ ረገድ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው።
እነዚህ አገር በቀል ዕውቀቶች ማኅበራዊ ትስስርን በማጠናከር ለትውልድ ግንባታ የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ የጎላ ሲሆን ለዘመናት በማህበረሰቡ እሴት ውስጥ በመስረፅም የበኩላቸውን በጎ ተፅዕኖ ማሳረፍ ችለዋል ፡፡
ከኢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም የታሪክና የማኅበረሰብ ጥናት ማዕከል ኃላፊ ዘላለም ተፈራ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ አለመግባባቶችን ወደ መግባባት የሚያመጡ በርካታ የሽምግልና፣ የአባ ገዳ እና የሲንቄ (ሀዳ ሲንቄ) የመሳሰሉ የዳበሩ እሴቶች ባለቤት መሆኗን አስታውሰዋል።
እነዚህ እሴቶችና ሥነ-ሥርዓቶች በዘፈቀደ በማንኛውም ቦታ የሚከናወኑ ሳይሆኑ፥ በባህላዊም ሆነ በሃይማኖታዊ አመለካከት ትልቅ ትርጉም፣ ክብርና ቦታ ባላቸው ሥፍራዎች እንደሚከናወኑ ኃላፊው ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰቦች በቋንቋና በባህል ተሳስረው ለዘመናት አብሮ በመኖራቸው ሳቢያ ባህሎችና ቋንቋዎች እርስ በእርስ ተወራርሰው በጋራ የመኖርና ተግዳሮቶችን የመሻገር ጥበቦችን መማማራቸውን ገልጸዋል።
በመሆኑም ልዩነቶቻችን ውበት ሆነው እንዲቀጥሉና አብሮነትን የሚያጠናክሩ የጋራ እሴቶች ላይ በትጋት የመሥራት ባህል ሊዳብር እንደሚገባ አሳስበዋል።
ለዚህም አገራዊ እሴቶቻችንን በመጠቀም ያጋጠሙ ችግሮችን በየደረጃቸው ለይቶ እልባት መስጠትና ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት እንደሚገባ ተናግረዋል።
በንፍታሌም እንግዳወርቅ
#ebc #ethiopianculture #socialcohesion #indigenousknowledge

16 days ago