ብረሽድ ባይ ቤቲ የውበት አካዳሚ ከ400 በላይ ሰልጣኞችን አስመረቀ
#ethiopia | ብረሽድ ባይ ቤቲ የውበት አካዳሚ በሰባተኛው ዙር የማሰልጠኛ መርሃ ግብሩ ያሰለጠናቸውን ከ400 በላይ ተማሪዎች በትላንትናው ዕለት አስመርቋል።
ተመራቂዎቹ በሜካፕ፣ በጥፍር አሰራር፣ በሽፋሽፍት ውበት (eyelash)፣ በኦምብሬና በፌሻል የውበት አጠባበቅ ዘርፎች የንድፈ ሃሳብና የተግባር ስልጠናቸውን በሚገባ ያጠናቀቁ ባለሙያዎች ናቸው።
የተቋሙ መስራችና ባለቤት ወ/ሮ ቤተልሔም እስክንድር በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ እንደገለጹት አካዳሚው ከተመሰረተ 13 ዓመታት ያለፉት ሲሆን ተማሪዎቹን በውበት ሙያ ማብቃት ብቻ ሳይሆን ራሳቸውን ችለው ወደ ስራ እንዲገቡ ለማስቻል ሰፊ እገዛ ያደርጋል።
በዚህም መሰረት ተማሪዎቹ በስልጠና ቆይታቸው የዲጂታል ማርኬቲንግ፣ የቪዲዮግራፊ፣ የፎቶግራፊና የህይወት ክህሎት ስልጠናዎችን በነጻ እንዲወስዱ ተደርጓል።
ይህም የራሳቸውን ስራ ፈጥረው ራሳቸውን በቀላሉ ማስተዋወቅ እንዲችሉ ትልቅ አቅም ይፈጥርላቸዋል።
ተመራቂዎቹ ከስልጠና በኋላ በቀጥታ ወደ ስራ እንዲሰማሩና የራሳቸውን ተቋም እንዲከፍቱ ለማድረግም አካዳሚው ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ እና ከከፍታ ጋር በመተባበር የብድርና የፋይናንስ አገልግሎት የሚመቻችበትን መንገድ ዘርግቷል።
በተጨማሪም ተቋሙ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት መስማት ለተሳናቸው ወገኖችና አቅም ለሌላቸው እናቶች ነጻ የስልጠና እድሎችን ሲሰጥ የቆየ ሲሆን በቅርቡ "ቢ ኮስሞቲክስ" የተሰኘ የራሱን የውበት ብራንድ ለመጀመር እንዲሁም የትራንስፖርት ችግርን ለመቅረፍ የኦንላይን የውበት ትምህርት ስልጠናዎችን ለማስጀመር በትጋት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

19 days ago