“ዕድሜ ለህልም እንቅፋት አይደለም”፦ የ62 ዓመቱ አባት ከልጃቸው ጋር የ12ኛ ክፍል ፈተናን እየወሰዱ ነው
*********************
ዕድሜ ለህልም መሳካት ማነቆ ሳይሆን ለቁርጠኝነት መለኪያ መሆኑን በተግባር እያሳዩ የሚገኙት የ62 ዓመቱ አቶ ዩሱፍ ኢብራሂም፣ በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የብዙዎችን ትኩረት ስበዋል።
ከሶማሊ ክልል ሲቲ ዞን ጎታ ቢቄ ወረዳ የመጡት አቶ ዩሱፍ፣ ከገዛ ልጃቸው ጋር በመሆን በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የፈተና አዳራሽ በመገኘት የዕውቀት ጉዟቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ።
አባትና ልጅ በአንድ የፈተና ጣቢያ መፈተናቸው ለፈተናው አዳራሽ ልዩ ድምቀት የፈጠረ ሲሆን፣ አቶ ዩሱፍ ከልጆቻቸውና ከልጅ ልጆቻቸው እኩያ ከሆኑ ወጣቶች ጋር ጎን ለጎን ተቀምጠው መፈተናቸው ታላቅ ክብርና ደስታ እንደሰጣቸው ይናገራሉ።
አቶ ዩሱፍ በዚህ ዕድሜያቸው ፈተናውን ለመውሰድ የወሰኑት የራሳቸውን ህልም ለማሳካት ብቻ ሳይሆን፣ በትምህርታቸው ተስፋ ለሚቆርጡ ወጣቶች አርአያ በመሆን መነቃቃትን ለመፍጠር ጭምር ነው።
“ትምህርት የሀገር ፍቅር መገለጫ ነው” የሚሉት አቶ ዩሱፍ፣ ለግለሰብም ሆነ ለሀገር እድገት ትምህርት ዋነኛው ቁልፍ መሆኑን በጽኑ ያምናሉ። ተማሪዎች በሙሉ በትምህርታቸው በርትተው በመማር፣ ነገ አመርቂ ውጤት በማምጣት ሀገራቸውን በታማኝነት ማገልገል እንዳለባቸውም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
የአቶ ዩሱፍ የዕውቀት ጉዞ በዚህ የ12ኛ ክፍል ፈተና ላይ የሚያበቃ አይደለም። ፈተናውን በከፍተኛ ውጤት በማለፍ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም በመግባት፣ የጀመሩትን የዕውቀት ጉዞ የመቀጠልና በዩኒቨርሲቲ የመመረቅ ትልቅ ራዕይ ሰንቀዋል።
የ62 ዓመቱ አባት ይህ ታሪካዊ ርምጃ፣ ትምህርት ለማንኛውም ዕድሜ የሰው ልጅ የላቀ መዳረሻ መሆኑን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል።
በቴዎድሮስ ታደሰ
#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያትማር #ethiopia #education

21 days ago