Logo
SeledaPost
አቶ ተወልደ ገብረማርያም የፓኪስታን አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሸሙ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ተወልደ ገብረማርያም፣ የፓኪስታን ብሔራዊ አየር መንገድን (PIA) ከገጠመው ከፍተኛ ኪሳራ አውጥተው ወደ ትርፋማነት እንዲመልሱ በዋና ሥራ አስፈጻሚነት መመረጣቸውን ብሉምበርግ እና አረብኒውስ ዘግበዋል።

ይህ ሹመት የተሰማው አየር መንገዱን ወደ ግል የማዛወሩ ሂደት የመጀመሪያ ምዕራፍ መጠናቀቁን ተከትሎ ሲሆን፣ "አሪፍ ሀቢብ ኮርፖሬሽን" የተባለው የግል ጥምረት የአየር መንገዱን የሥራ አመራር ቁጥጥር ተረክቧል።

👉አዲሶቹ ባለቤቶች የአየር መንገዱን የፋይናንስ አቅም ለማጠናከር፣ የበረራ አውሮፕላኖችን ለማዘመንና የበረራ መዳረሻዎችን ለማስፋፋት በመጀመሪያ ዙር 80 ቢሊዮን የፓኪስታን ሩፒ ( ወጪ አድርገዋል።

አቶ ተወልደ ገብረማርያም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በአፍሪካ ግዙፍና ስኬታማ አየር መንገድ በማድረግ ረገድ የነበራቸው ዓለም አቀፍ ዝና እና ልምድ ለዚህ ሹመት እንዳበቃቸው ተገልጿል።

👉ባለሀብቶቹ በአጠቃላይ 180 ቢሊዮን ሩፒ ለኢንቨስትመንት ያቀዱ ሲሆን፣ የአቶ ተወልደ መመረጥ አየር መንገዱን በክልላዊና በዓለም አቀፍ የኢንዱስትሪ ገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ ለማድረግ ለተያዘው ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ወሳኝ መሆኑ ታምኖበታል።

በአሁኑ ወቅት የአቶ ተወልደ ሹመት በይፋ ከመታወጁ በፊት የተለመደው የመንግስት የጸጥታ ማጣሪያ እየተከናወነ መሆኑን የአየር መንገዱ የሥራ ኃላፊዎች ማረጋገጣቸውን ብሉምበርግ እና አረብ ኒውስ ዘግበዋል፡፡

Seledadotio
Seledadotio
24 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.