የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የ2018 የክረምት በጎ ፈቃድ ነጻ ህክምናን በይፋ ጀመረ
#ethiopia | የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ የ2018 የክረምት በጎ ፈቃድ ነጻ ምርመራ እና የህክምና አገልግሎትን በይፋ ጀመረ።
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ በተካሄደው መርሐግብር ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ በመድረኩ የመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት " የክረምት ወራት በሀገራችን የምንረዳዳበት እና የምንደጋገፍበት ወቅት ነው ብለዋል።
ያለንን ውስን ሀብት በመጠቀም ሀገራችንን ማልማት ይጠበቅብናል ያሉት ክብርት ወ/ሮ ሎሚ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመሳተፍ ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች እና በጎ ፈቃደኞች በምክር ቤቱ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አነሳሽነት የተጀመረው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሁን ላይ ለሌሎች ሀገራት ተምሳሌት የሚሆንበት ደረጃ ላይ መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በመድረኩ ተናግረዋል። የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን በጤና ስርዓት ውስጥ በማካተት ባለፈው አመት ብቻ ለ15 ሚሊዮን ዜጎች ነፃ የህክምና አገልግሎት ማቅረብ መቻሉንም ግልጸዋል።
በክረምት ወራት በጎ ፈቃድ ብቻ ባለፈው ክረምት 176,000 ዩኒት ደም መሰብሰቡን እና የህክምና መሳሪያዎች ጥገና በማካሄድ ሃብትን ከብክነት ማትረፍ መቻሉንም አክለዋል።
የዚህ አመት የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት ከሀገር ግንባታ ጋር በማያያዝ የሚካሄድ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ገልጸዋል በጎነት ለጤናው ዘርፍ የዘወትር ስራ መሆኑን ጠቁመው በዚህ ክረምት እስከ 20 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን ተናግረዋል።
ለቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የክረምት በጎፈቃድ አገልግሎት ድጋፍ እያደረጉ ለሚገኙ ተቋማት እና የግል ሆስፒታሎች ምስጋና ያቀረቡት የሆስፒታሉ ፕሮቭኦስት ዶ/ር ሙሉቀን ተስፋዬ: ሆስፒታሉ ከመሰረቱ ማህበረሰቡን ማዕከል አድርጎ የተቋቋመ መሆኑን አስታውሰዋል።
በመርሃ ግብሩ የህዝብ ተዋካዮች ምክር ቤት የጤና ማህበራዊ ልማት፣ ባህል እና ስፖርት ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የጤና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች፣ የግል ሆስፒታል ኃላፊዎች፣ የሆስፒታሉ አመራር እና ተግልጋዮች የተሳተፉ ሲሆን፣ ነጻ የጤና ምርመራ፣ የምክርና ህክምና አግልግሎት መስጠት ተጀምሯል።
በተጨማሪም በዚህ ክረምት መርሃ ግብር የሆስፒታሉን ድንገተኛ የህክምና አገልግሎት መስጫ ክፍልን በአዲስ መልክ ለመገንባትና ለማደራጀት የሚያስችል ስራ የተጀመረ ሲሆን ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ እና በሆስፒታሉ እየተሰጠ የሚገኘው አገልግሎት ጉብኝት ተካሂዷል።
Ministry of Health,Ethiopia
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#stpaulshospital #sphmmc
#volunteermedicalservice
#freehealthcare #ethiopia
#healthcareforall

24 days ago