''አትመጣም ወይ ማርቆስ ከተድላው ከተማ
ቢሻህ በአውሮፕላን ቢሻህ በሎንቺና''
📌የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ ተመረቀ፤ ለከተማዋ የኢንዱስትሪ አብዮት በር ከፈተ
#ethiopia | ለበርካታ ዓመታት በናፍቆት ሲጠበቅ የነበረው የደብረ ማርቆስ ንጉስ ተክለ ሃይማኖት አውሮፕላን ማረፊያ ራዕዩን ዕውን አድርጎ በዛሬው እለት በይፋ ተመርቆ ሥራ ጀምሯል።
የአውሮፕላን ማረፊያው አገልግሎት መጀመር ለከተማዋና ለአካባቢው ከፍተኛ የኢኮኖሚ መነቃቃትን ይዞ የመጣ ሲሆን በቀጣይም በከተማዋ ላይ ትልቅ የኢንዱስትሪ አብዮት ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።
ይህ መደበኛ የሥራ መጀመሪያ ከዚህ ቀደም ተቀዛቅዞ የነበረውን የከተማዋን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ በማነቃቃት አልሚ ባለሀብቶች ያለምንም ስጋት መጥተው እንዲያለሙ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።
ከአሚኮ እንደሰማነው ከሆነ በአውሮፕላን ማረፊያው የሙከራ በረራ ወቅት ትልልቅ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች መምጣት የጀመሩ ሲሆን አሁን ደግሞ የውጭ ባለሀብቶችም ጭምር መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ በርከት ብለው መምጣት ጀምረዋል።
ከዚህም ባሻገር የአውሮፕላን ማረፊያው አገልግሎት አምራቾች ምርቶቻቸው ሳይበላሹ በአጭር ጊዜ ለገበያ እንዲያቀርቡ በማስቻል የምርት እጥረትን በዘላቂነት ይረዳል፤ ጥራትንም በእጅጉ ይጨምራል።
ከኢንቨስትመንት ባለፈ የከተማዋን የቱሪዝም ዘርፍና አጠቃላይ ኢኮኖሚ በከፍተኛ ደረጃ የሚያነቃቃው ይህ ዕድል ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ይዞ የመጣ በመሆኑ ባለሀብቶች መጥተው በከተማዋ እንዲያለሙ የከተማው አስተዳደር ጥሪውን አቅርቧል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

24 days ago