Logo
FastMereja
"እናቴን በ8 አመቴ፣ አባቴን በ10 አመቴ በሞት ተነጠቅኩ"

ገና በ8 አመቴ ክፉ ደጉን ሳላውቅ ጠንካራ እናቴን አጣሁ፣ 10 አመት ሲሞላኝ ደግሞ እናትም አባትም ሆኖኝ የነበረውን አባቴን በሞት ተነጠኩ።

በነዚህ የተረገሙ ቀናት እኔም ወንድም እህቶቼም ወላጅ አልባ ሆንን። ሙሉ ቤተሰቤን ህይወት ክፉኛ ፈተነችን። በብዙ ስቃይ ውስጥ ቢሆንም ባለኝ ትንሽ ተስፉ አድጌ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገባው። በፈተና ውስጥም ቢሆን ከፍተኛውን ውጤት ይዤ በመካኒካል ኢንጅነሪንግ ከ 15 ኮርሶች በላይ A+ አምጥቼ ተመረኩ።

በ 2010 ዓም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ መምህር ሆኜ ተቀጠርኩ። በ 2013 ደግሞ በተርማል ኢንጅነሪንግ ከፍተኛውን ውጤት ይዤ ከአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተመርቄ አሁንም ድረስ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ እያስተማርኩ እገኛለው። ከ 200 በላይ ተማሪዎችንም አስተምሬ አስመርቅያለው።

ከአካዳሚክ ህይወቴ ጎን ለጎን ለ 5 አመት ለተለያዩ የዲጂታል ሚዲያዎች የስክሪፕት መፃፍ እና Audio Narrator ስራን ሰርቼ ከ 3ሺ በላይ ዜና ስክሪፕት ፅፌያለው። ይሄን ልምድም ተጠቅሜ በቲክቶክ 2.5 ሚሊዮን ተከታይ ማፍራት ችያለው። ተመልካቾቼም ሳጠፋ ኮርኩመው ሳለማ አመስግነው አብረውኝ አሉ።

ከቲክቶኩ ባሻገር በብስራት ቲቪ የ"ባዮ አለም" ፕሮግራም አዘጋጅ ሆኜ እንዲሁም በትርታ ኤፍኤም ላይ ፕሮግራም ይዤ ሰርችያለው። ከሁለት አመት በፊት ደግሞ BN Advertising and Events የተሰኝ ድርጅት መስርተን ብዙ ስራዎችን ሰርተናል። እኔም ወንድም እና እህቶቸም በብዙ ተፈትነናል፣ ወደፊትም እንፈተናለን። ግን እናልፈዋለን።

አሁን የልጅ አባትም ሆኛለው መድሐኒያለም ክበሩን ይውሰድ።
ብሩክ ጫላ (ብሩክ ኒውስ)

27 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.