Logo
YenetaTube
የኢትዮጵያ መድኃኒት የማምረት አቅም 45 በመቶ ደረሰ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መድኃኒት የማምረት አቅም ከነበረበት 4 በመቶ ወደ 45 በመቶ ማደጉን አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው።

በዘርፉ የተመዘገበው ለውጥ የመድኃኒት ጥራት ቁጥጥር ሥርዓቱን በማሻሻሉ የመጣ ውጤት እንደሆነ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የመድኃኒት ቁጥጥር ኤጀንሲ ደረጃን በማሟላት ከአፍሪካ ሦስተኛ ደረጃ መያዟ ተነግሯል። ይህ ዕድገት በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶች ለውጭ ገበያ የመቅረብ ዕድላቸውን ከፍ አድርጓል ተብሏል።

የተሻሻለው የቁጥጥር ሥርዓት የማምረት አቅሙን በማሳደግ የኤክስፖርት ተወዳዳሪነትን እያረጋገጠ ነው።

መንግሥት በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት ለሕክምና መሣሪያዎች ከ60 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጉም ተጠቅሷል።

አሁን ላይ አብዛኛው የሕክምና መሣሪያ ከውጭ አገር በግዢ እንደሚገባ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚንስትሩ በቀጣይ 5 ዓመታት ዘመናዊ የሕክምና ተቋማትን በመገንባት የማምረት አቅሙን የበለጠ ለማሳደግ ታቅዷል ብለዋል።

አሐዱ ሬዲዮ

29 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.