ሀገራዊ አንድነትን ማጠናከሪያው ገመድ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት …
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሙና አህመድ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሀገራዊ አንድነትን፣ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን የማጠናከር ትልቅ ዓላማ አለው አሉ።
ሚኒስትር ዴኤታዋ ከፋና ፖድካስት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከቀጥተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ያለፈ ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው አብራርተዋል።
ይህም በዜጎች መካከል የእኔነትና የወገንተኝነት ስነ-ልቦናን የሚያዳብር በመሆኑ ለሀገር ያለው ፋይዳ የጎላ ነው ብለዋል።
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ንቅናቄ በመንግሥት ደረጃ በክረምትና በበጋ ተከፋፍሎ እንደሚመራ ገልጸው፤ ዓላማው በጎ ፈቃደኝነትን የማህበረሰቡ ቋሚ ባህል ማድረግና የሀገሪቱን ህብረ ብሔራዊ አንድነት ይበልጥ ያጠናክራል ነው ያሉት።
“አንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት” በሚል አሰራር በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በመንግሥት ያልተሸፈኑ የልማትና ማህበራዊ አገልግሎቶችን ለመሸፈን ስራዎች መጀመራቸውንም ገልጸዋል።
ንቅናቄው ቁሳዊ ፍላጎቶችን ከመሙላት ባለፈ፣ የሀገር ፍቅር የሚያዳብር፤ የሕሊና ደስታን የሚያስገኝና መላውን ህዝብ በአንድ የጋራ ዓላማ ስር የሚያስተባብር ትልቅ የአንድነት ማሰሪያ ገመድ መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይም ወጣቶችን በማስተባበር የሚከናወኑ የወሰንና የድንበር ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ ስራዎች፣ በተለያዩ አካባቢዎች በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መካከል መቀራረብንና ፍቅርን በመፍጠር ረገድ መተኪያ የሌለው ሚና እያበረከቱ እንደሚገኙ አብራርተዋል።
ይህንኑ መልካም እሴት ይበልጥ ለማሳደግና የወጣቶችን ትስስር ለማላቅ ታስቦ የተዘጋጀው የዘንድሮው የወሰን ተሻጋሪ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ዛሬ በሀዋሳ ከተማ በይፋ ተጀምሯል፡፡
በቅድስት ዘውዱ
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሙና አህመድ ከፋና ፖድካስት ጋር ያደረጉትን ቆይታ ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://www.youtube.com/wa...

29 days ago