(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ግብፅ ለፊፋ ማመልከቻ ስታስገባ ጆሴ ሞሪንሆ ‹‹የጠራራ ፀሀይ ዝርፊያ ነው›› አሉ፡፡ የግብፅ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ሀኒ አቦሪዳ ከአርጀንቲና ጋር በተደረገው ግጥሚያ ሙሉ ምርመራ እንዲደረግበት ለፊፋ ማመልከቻ ማስገባታቸውን አስታወቁ፡፡ ፌዴሬሽኑ በማመልከቻቸው በጨዋታው ላይ የተፈጠረው የዳኝነት ስህተቶች ግብፅ ከውድድሩ እንድትወጣ ቀጥተኛ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን ገልጿል፡፡
ዘለግ ያሉ ሀሳቦችን በያዘው በዚህ ማመልከቻው ከጠቀሳቸው ሀሳቦች ውስጥ ግብፅ ያገባችው ሁለተኛ ጎል በቫር ውሳኔ መሻሩ፣ በጨዋታው መጨረሻ ላይ ለግብፅ ፍፁም ቅጣት ምት አለመሰጠቱ፣ አርጀንቲና የማሸነፊያውን ጎል ከማግባቷ በፊት በመሀመድ ሳላህና ሀምዲ ፋቲ ላይ የተሰራው ጥፋት በቫር አለመታየቱና በአጠቃላይ በጨዋታው የቫር አሰራር ወጥነት የሌለው መሆኑ ይገኙበታል፡፡ በመሆኑም በዋና ዳኛው ፍራንሲስ ሌቲክሲየር፣ በረዳቶቻቸውና በቫር ተቆጣጣሪ አባላት ላይ ፊፋ ጥብቅ ምርመራ እንዲያደርግ የጠየቀው ፌዴሬሽኑ የምርመራው ውጤት እስከሚጠናቀቅ ድረስ የአለም ዋንጫ ጨዋታዎች እንዲቋረጡም አሳስቧል፡፡
የግብፅ ብሄራዊ ቡድን ተጨዋቾች ባለፈው የአለም ዋንጫ ሻምፒዮን በነበሩት አርጀንቲናዎች ላይ ላሳዩት የጨዋታ የበላይነትና ብቃት ‹‹ጀግኖች›› በሚል ያወደሳቸው ፌዴሬሽኑ በተፈጠረው የዳኝነት ስህተት ቡድኑ የበላይነቱን ማስቀጠል ባለመቻሉ ደጋፊዎችን ይቅርታ ጠይቋል፡፡ ፊፋ በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን የሰጠው መልስ የለም፡፡ ይሁንና የግብፅ ብሄራዊ ቡድን እንዲህ አይነት ማመልከቻዎችን ለፊፋ ሲያስገባ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ ከዚህ ቀደም በዳኞች ላይ ምርመራ እንዲደረግና ውድድሩ ምርመራው እስኪጠናቀቅ እንዲቋረጥ ጥያቄ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም ፊፋ ግን የወሰደው እርምጃ የለም፡፡
በ2018 የአለም ዋንጫ ወቅት በምድብ ጨዋታ ግብፅ ከአዘጋጇ ሩሲያ ጋር ባደረገችው ግጥሚያ ከተሸነፈች በኋላ የዳኛው ውሳኔ እንዲመረመር ጠይቃ የነበረ ሲሆን ፊፋ ግን ጥያቄው ቸል ማለቱ ይታወሳል፡፡ እንዲሁም በ2002 አለም ዋንጫ ጣሊያን በ16ቱ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ በደቡብ ኮሪያ መሸነፏን ተከትሎ የዳኝነት ምርመራ ጠይቃ ምንም እርምጃ ሳይወሰድ ቀርቷል፡፡ የግብፅ አሰልጣኝ የሆኑት ሆሳም ሀሰን በሰጡት መግለጫ ቡድናቸው በሜዳ ውስጥና ከሜዳ ውጭ ድል ወደአርጀንቲና እንዲሆን በተደረገው ሴራ ሰለባ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ሲናሩም ‹‹እኛ የተሻልን የነበርን ከመሆናችንም በላይ ተጋጣሚያችን ላይ ጫና ፈጥረን ነበር፡፡ ዳኝነቱ ግን ፍትሀዊ አልነበረም፡፡ ግባችንን ለምን እንደተከለከልን አላውቅም›› ብለዋል፡፡
ጨምረውም ‹‹የአለም ዋንጫ የማርኬቲንግ ጉዳይ ሆኗል፡፡ እነሱ በቻሉት መጠን ሜሲ በውድድሩ ላይ እንዲቆይ ፈልገዋል፡፡›› በማለት ገልፀዋል፡፡ የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ በበኩላቸው ዳኛው የሰጡትን ውሳኔ ‹‹በጠራራ ፀሀይ የተፈፀመ ዝርፊያ ነው›› በማለት ገልፀውታል፡፡ ሲናገሩም ‹‹ግብፆች ሁለት ለዜሮ እየመሩ በነበረበት ወቅት ሲጋጠሙ የነበሩት በሜዳ ላይ የነበሩትን 11 ተጨዋቾች ብቻ አልነበረም፡፡ በስታዲየሙ የነበረውን ፉጨትና የቫር ክፍሉን ጭምር እየተጋጠሙ ነበር፡፡ በአጠቃላይ የውድድሩን ስክሪፕት ለማሸነፍ ታግለዋል›› በማለት አስታውቀዋል፡፡

30 days ago