Logo
Getu Temesgen
በአዲስ አበባ የቤት ኪራይ ዓመታዊ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% እንዲሆን ተወሰነ

📌10,000 ብር (ወርሃዊ ኪራይ) * 11.5% (አዲሱ ስሌት) = 1150 ብር (ጭማሪ)
#​Ethiopia | ​የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር በመዲናዋ በኪራይ ገበያው ላይ የሚስተዋሉ ሕገ-ወጥና ዘፈቀዳዊ አሠራሮችን ለመግታትና የዜጎችን የኑሮ ጫና ለመቀነስ ያስችላል ያለውን አዲስ መመሪያ ይፋ አድርጓል።

ቀደም ሲል በወጣው የቤት ኪራይ ቁጥጥር አዋጅ መሠረት ለ2019 በጀት ዓመት የሚተገበረው ፍትሐዊ የቤት ኪራይ ዓመታዊ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ መጽደቁን የከተማዋ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።

ይህንን ውሳኔ ተከትሎም በመላው ከተማዋ የሚገኙ የግል መኖሪያ ቤቶች የአከራይ-ተከራይ አዲስ የውል ዕድሳት ምዝገባ ከዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ፅሕፈት ቤቶች በይፋ መተግበር ጀምሯል።

​ቢሮው እንዳመለከተው ይህ የዋጋ ማስተካከያ ውሳኔ በዘፈቀደ የተወሰነ ሳይሆን በከተማዋ ሰፊ ሳይንሳዊ ጥናት ተካሂዶ የነዋሪውን እውነተኛ የመክፈል አቅም ባገናዘበ መልኩ የተዘጋጀ ነው።

ቢሮ'ው ''አዲሱ አሠራር በአንድ በኩል አከራዮች ወቅቱንና የኢኮኖሚ ሁኔታውን ያገናዘበ ፍትሐዊ ገቢ እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ተከራዮች ከገቢያቸው ጋር የተመጣጠነ ኪራይ በመክፈል ከተደጋጋሚ መፈናቀልና ከሥነ-ልቦና ስጋት ድነው የተረጋጋ ሕይወት እንዲመሩ ያደርጋል'' ብሏል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.