(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ አሜሪካ በኢራን የነዳጅ ሽያጭ ላይ ተጥሎ የነበረውን ማዕቀብ በጊዜያዊነት የሚያነሳውን ውሳኔ በመሰረዝ የመግባቢያ ሰነዱን አንቀጽ 10 በግልጽ ጥሳለች ሲል ከሰሰ። ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ፣ የአሜሪካ ግምጃ ቤት የወሰደውን እርምጃ ሰኔ 18 የተፈረመውን የመግባቢያ ሰነድ የጣሰ ነው በማለት አውግዞታል።
ስምምነቱ ከተፈረመ ከ20 ቀናት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የተላለፈው ይህ ውሳኔ፣ የአሜሪካ አስተዳደር ታማኝነት የጎደለው መሆኑን ያሳየ እና ሊታመን የማይችል መሆኑን ያረጋገጠ ነው ሲል ሚኒስቴሩ ገልጿል። በተጨማሪም፣ ዋሽንግተን በቀጥታም ሆነ እስራኤል በሊባኖስ ላይ በምትወስደው እርምጃ በተዘዋዋሪ የመግባቢያ ሰነዱን ክፍሎች ደጋግማ መጣሷን በመግለጫው በክስ መልክ ተነስቷል።
በሌላ በኩል የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ በኢራን ኢላማዎች ላይ ተከታታይ እና ጠንካራ ጥቃቶችን መፈጸሙን የሚያሳይ መግለጫ አውጥቷል። ዕዙ ከዚህ ባለፈ የሰጠው ዝርዝር መረጃ ባይኖርም፣ በኢራን ተከታታይ ጥቃቶች እና በአሜሪካና ኢራን የድርድር ማዕቀፍ ውስጥ የተካተተውን የመግባቢያ ሰነድ ኢራን ደጋግማ መጣሷ እጅግ እንዳሳሰበው አስታውቋል።
ከዚህ ቀደም የአሜሪካ ግምጃ ቤት፣ በመግባቢያ ሰነዱ መሰረት ኢራን ነዳጅ ወደ ውጭ እንድትልክ ፈቅዶ የነበረውን ማዕቀብ የማንሳት ውሳኔ ሰርዞ ነበር። ግምጃ ቤቱ እንዳብራራው ከሆነ ይህ የማዕቀብ ማንሳት ውሳኔ በቅድመ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ እንደነበር እና ኢራን እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች ባለማሟላቷ ስረዛው ተፈጽሟል። በመሆኑም የነዳጅ ማዕቀቦቹ ከሐምሌ 17 ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ እንደሚመለሱ ይጠበቃል ብሏል።

1 month ago