Logo
Getu Temesgen
*ደሴቲቱ ለሽያጭ የቀረበች አይደለችም፦ዴንማርክ

*ለእኛ ደግሞ ዋነኛ የብሔራዊ ደህንነት አጀንዳችን ነው፦አሜሪካ
#ethiopia | ፕሬዚዳንት ትራምፕ ግሪንላንድ በአሜሪካ ቁጥጥር ስር መሆን አለባት በማለት የቀድሞ አቋማቸውን በድጋሚ አንጸባርቀዋል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግሪንላንድ በዴንማርክ ቁጥጥር ስር መሆን እንደሌለባት እና በአሜሪካ ስር መተዳደር እንደሚገባት በድጋሚ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

በአንካራ እየተካሄደ በሚገኘው የኔቶ (NATO) ጉባኤ ላይ ከተርክዬ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር የመከሩት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ግሪንላንድ የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት አጀንዳ መሆኑን ገልጸዋል።

የዴንማርክ ባለስልጣናት በበኩላቸው ደሴቲቱ "ለሽያጭ የቀረበች አይደለችም" የሚል ጠንካራ አቋማቸውን በድጋሚ አንጸባርቀዋል።

ግሪንላንድ በሩሲያ እና በቻይና መርከቦች የተከበበች መሆኗ ለአሜሪካ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታዋ የጎላ መሆኑን አስረድተዋል።

ይህ የፕሬዚዳንቱ ንግግር በዋሽንግተን እና በኮፐንሃገን መካከል ውጥረት እንዲፈጠር አድርጓል።

የግሪን ላንድ ጉዳይ በአሁኑ ወቅት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እየታየ መሆኑን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #apnewsgreenlandissue #americadenmark

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.