Logo
Getu Temesgen
ቤልጂየም አሜሪካን 4-1 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜን ተቀላቀለች
#ethiopia | በ23ኛው የዓለም ዋንጫ የ16ቱ ሀገራት የጥሎ ማለፍ ውድድር ቤልጂየም የጣምራ አዘጋጅ አሜሪካን 4 ለ1 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜ ማለፍ ችላለች።

በሲያትል ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቻርለስ ዲ ኬተላረ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር የድሉ ዋና ተዋናይ ሆኗል። ሃንስ ቫኔከን እና ሮሜሉ ሉካኩም ተጨማሪ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር የቤልጂየምን ድል አረጋግጠዋል።

አሜሪካ በጨዋታው ደካማ ብቃት ሲያሳይ ብቸኛ ግቧን በማሊክ ቲልማን አስቆጥራለች።

በዚህ ውጤት የ2026 ዓለም ዋንጫ ሦስቱም የጣምራ አዘጋጅ ሀገራት ማለትም ካናዳ፣ ሜክሲኮ እና አሜሪካ በ16ቱ ዙር ከውድድሩ ውጪ ሆነዋል።

ቤልጂየም በሩብ ፍጻሜ በሌላ አስደናቂ ጨዋታ ፖርቱጋልን 1 ለ0 በማሸነፍ ያለፈችውን ስፔን ትገጥማለች።
#worldcup2026 #belgium #usa #quarterfinal #football #getutemesgenmedia

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.