(ዘ-ሐበሻ ዜና) ለታሊ መክረ ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል ያደረገችው ጉዞ በበርካታ ፈተናዎች የታጀበ ቢሆንም፣ የተሻለ የወደፊት ህይወትን ለመገንባት ባላት ጽናት እና ቆራጥነት ዛሬ ላይ ትልቅ የስኬት ማማ ላይ መድረስ ችላለች።
ወደ አዲሱ ህይወት ያደረገችው የሽግግር ጉዞ የጀመረው ገና በ5 ዓመቷ በ1997 (እ.ኤ.አ) ነበር። በመጀመሪያዎቹ ዓመታት ቤተሰቦቿ በአከር በሚገኝ የስደተኞች መቀበያ ማዕከል ውስጥ ይኖሩ የነበረ ሲሆን፣ ታናናሽ እህት እና ወንድሟም የተወለዱት እዚያው ነው። በኋላም ወደ ኔታንያ ከተማ ተዘዋውረዋል። በእስራኤል የነበራቸው አዲስ ህይወት ቀላል አልነበረም። ወላጆቿ የዕብራይስጥ ቋንቋ የማይናገሩ በመሆናቸው ቤተሰቡን ለማስተዳደር ለረጅም ሰዓታት ይለፉ ነበር። ታሊ ይህንን ጊዜ ስታስታውስ፣ "እንደ ታላቅ ልጅ ታናናሾቼን እከባከብ እንዲሁም በወላጆቼ እና በማህበረሰቡ መካከል ያለውን የቋንቋ እና የባህል ክፍተት ለመሙላት እረዳ ነበር፤ ትልቅ ኃላፊነትም ወድቆብኝ ነበር" ትላለች።
እነዚህ ሁሉ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ ታሊ ትምህርቷን እጅግ ትወድ ስለነበር በተለይም በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሂሳብ (STEM) የትምህርት ዘርፎች ላይ ከፍተኛ ጥረት አድርጋለች። ለትምህርት ቤቷ የላቀ ውጤት ወላጆቿ፣ የራሷ ጽናት እና በእሷ ያመኑ መምህራኖቿ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳደረጉ ትናገራለች። በከፍተኛ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለች በቴል አቪቭ ዩኒቨርሲቲ እና በዌይዝማን የሳይንስ ኢንስቲትዩት በሚመራ ሀገር አቀፍ የሳይንስ ማበልጸጊያ ፕሮግራም እንድትሳተፍ ተመርጣ፣ በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቃለች።
በ18 ዓመቷ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት (IDF) የትምህርት ውጤቷን በመመልከት ውትድርናዋን ከመጀመሯ በፊት የሁለት ዓመት የተግባር ምህንድስና (Practical Engineer) ፕሮግራም እንድትማር መክሯታል። ፕሮግራሙን ካጠናቀቀች በኋላ በመረጃ ደህንነት የቴክኖሎጂ ክፍል ውስጥ ተመድባ በቴክኖሎጂ እና በምህንድስና ዘርፍ ጠቃሚ የሙያ ልምድ አግኝታለች።
የሶስት ዓመቱን የውትድርና አገልግሎት ካጠናቀቀች በኋላ በኔጌቭ በሚገኘው የቤን-ጉርዮን ዩኒቨርሲቲ በኤሌክትሪካል እና ኮምፒውተር ምህንድስና ትምህርቷን ለመቀጠል ተቀባይነት አገኘች። ሆኖም የአራት ዓመቱን የትምህርት ወጪ እንዴት እንደምትሸፍን ተጨንቃ ነበር። ነገር ግን 'አቲዲም' (Atidim) ከተባለ ፕሮግራም የትምህርት ክፍያ፣ የኑሮ ወጪ እና ላፕቶፕን ጨምሮ የተሟላ ድጋፍ በማግኘቷ ስጋቷ ተቀርፎ ትምህርቷን በስኬት አጠናቃለች።
በፕሮግራሙ ማበረታቻ መሰረት በዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ በእስራኤል ቀዳሚ የደህንነት ቴክኖሎጂ ኩባንያ በሆነው ኤልቢት ሲስተምስ ውስጥ የቦርድ ዲዛይን ኢንጂነር በመሆን ሰርታለች። ከተመረቀች በኋላ በዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ ከተዋወቀችው የኮንስትራክሽን ኢንጂነር ባለቤቷ ጋር ትዳር መስርታ በሀዴራ ከተማ መኖር የጀመረች ሲሆን፣ እ.ኤ.አ በ2022 በዓለም አቀፍ ደረጃ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የኮምፒውተር ስራዎች ቀዳሚ ወደሆነው ኤንቪዲያ (Nvidia)ኩባንያ ተቀላቅላለች።
በአሁኑ ወቅት የሶስት ልጆች እናት የሆነችው የ34 ዓመቷ ታሊ፣ በከፍተኛ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ውስጥ ያላትን ስራ እና የእናትነት ኃላፊነትን ማመጣጠን ፈታኝ ቢሆንም ኤንቪዲያ ለሚሰሩ እናቶች የሚያደርገው ድጋፍ ልዩ መሆኑን ትናገራለች። ታሊ የኤሌክትሪካል ኢንጂነር ለሆነችው ታናሽ እህቷም ሆነ በዘርፉ መሰማራት ለሚፈልጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወጣት ሴቶች ትልቅ አርአያ ሆናለች።
"በተለይ በኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ልጃገረዶች በርካታ እድሎች እንዳሏቸው እና የማደግና የስኬት አቅም እንዳላቸው እንዲያውቁ እፈልጋለሁ" በማለት መልዕክቷን ታስተላልፋለች። ለመጀመሪያ ጊዜ የዩኒቨርሲቲ ምሩቅ እና ኢንጂነር የሆነችው ታሊ "ሊረዱ የሚችሉ ድንቅ ሰዎች አሉ። በራስዎ ላይ እምነት እና ቆራጥነት ካለዎት ማንኛውም ነገር ይቻላል" የሚል አበረታች መልዕክት ለወጣቶች ታካፍላለች።
በአዲሱ ሀገር ካጋጠማት የልጅነት ፈተና ተነስታ በእስራኤል የከፍተኛ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ውስጥ እስከደረሰችበት የስኬት ማማ ያደረገችው ጉዞ፣ ትምህርት፣ ጽናት እና ትክክለኛ ድጋፍ ሊፈጥሩ የሚችሉትን ዕድል በጉልህ የሚያሳይ ነው።

1 month ago