እንግሊዝን ስጋት ላይ የጣለው የአዝቴካ ስታዲየም ከፍታና የዲየጎ ማራዶና የእጅ ግብ ታሪክ።
#ethiopia | በአለም ዋንጫ በ16 ጥሎ ማለፍ ከሚጠበቁ ጨዋታዎች መካከል የጥምር አዘጋጇ ሜክሲኮ ከእንግሊዝ የሚያደርጉት ፍልሚያ ነው። ጨዋታው በታሪካዊው አዝቴካ ስታዲየም ይደረጋል። ይህ ስታዲየም 87523 ተመልካቾች መያዝ የሚችል ፣ በላቲን አሜሪካ በግዝፈቱ ተወዳዳሪ የሌለውና በአለም 8ኛው ትልቅ ስታዲየም ነው።
አዝቴካ ስታዲየም የ1970 እና 1986 ሁለት የአለም ዋንጫ ፍጻሜዎችንም አስተናግዷል።ይህ ስታዲየም ከባህር ጠለል በ2240 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን የብዙ እግር ኳስ ቡድኖችን ትንፋሽ ያቆመ ነው። የእንግሊዝና ሜክሲኮን ጨዋታ ከሜዳ ላይ ፍልሚያው ባሻገር መነጋገሪያ እንዲሆን ያደረገው ቀዳሚ ጉዳይም ነው።
ባለ ሜዳዋ ሜክሲኮ በዚህ ከፍታና ግዙፍ ስታዲየም ካደረገቻቸው 89 የነጥብ ጨዋታዎች የተሸነፈችው 2 ጊዜ ብቻ ነው። ባለፉት 22 ጨዋታዎች ደግሞ አንዱንም አልተሸነፈች።16 ጊዜ አሸንፋ በ6ቱ አቻ ተለያይታለች።
እንግሊዝ በ32ቱ ጥሎ ማለፍ ሮብ እለት በዲሞክራቲክ ኮንጎ ተፈትና 2 ለ 1 ስታሸንፍ የተጫወተችበት የአትላንታ ስታዲየም ከፍታ 300 ሜትር ብቻ ነበር። አርብ እለት ደግሞ ወደ ሜክሲኮ ተጉዘዋል። ለጨዋታ ከተለመደው ጊዜ አንድ ቀን ቀድመው ቢደርሱም ትንፋሽ የሚያቆመውን አየር ለመልመድ በቂ አልሆነም።
ከልክ ያለፈ ከፍታ ተጫዎቾችን ለኦክስጂን እጥረት ይዳርጋል። ሰውነታቸው አየሩን ወደ ሴሎቻቸው የመግፋት አቅም እንዲያጣ ያደርጋል ይላሉ ባለሙያዎች።
ይህ ደግሞ ተጫዎቾቹ የልብ ምታቸው እንዲፈጥን ፣ ትንፋሽ እንዲያጥራቸው ፣ በፍጥነት የፈሳሽ እጥረት እንዲገጥማቸው ፣ ከፍተኛ ድካም ውስጥ እንዲገቡና የማገገሚያ ጊዜያቸውን እንዲራዘም ያደርጋል።
በተጨማሪም የአየር እጥረቱ ኳስ በሚሞከርበትና ለቡድን አጋር በሚሻማበት ጊዜ ፍጥነትና ከፍታውን የማስቀየር አቅም አለው ተብሏል። ስታዲየሙ ሁሉንም ተጫዎቾች ተጨማሪ አቅም የሚጠይቅ ቢሆንም የግብ ጠባቂዎችን ፈተና ያበዛል ተብሏል። ይህ እግር ኳሳዊ ፈተና ግን ለእንግዳዋ እንግሊዝ ብቻ ሳይሆን ለባለቤቷ ሜክሲኮም የሚያጋጥም ነው።
ሜክሲኮ በአዝቴካ ያላት ታሪካዊ የበላይነት ብቻ ሳይሆን በዚሁ አለም ዋንጫ ካደረገቻቸው 4 ጨዋታዎች 3ቱን ተጫውታበት 3ቱንም አሸንፋለች። በመክፈቻው ደቡብ አፍሪካን 2 ለ 0 ፣ ቸክ ሪፐብሊክን 3 ለ 0 በምድብ ፣ በ32 ጥሎ ማለፍ ደግሞ ኢኳዶርን 3 ለ 0 ድል አድርጋለች። በ2ኛው የምድብ ጨዋታ ደቡብ ኮሪያን 1 ለ 0 የረታችበት ጨዋታ ብቻ ከአዜቲካ ውጭ ተደርጓል። ሜክሲኮ ያደረገቻቸውን 4ቱንም ጨዋታዎች ስታሸንፍ 8 ግቦችን አስቆጥራ አንድም ሳይቆጠርባት በመውጣት የማጥቃትና የመከላከል አቅሟን አስመስክራለች።
የሶስቱ አናብስት አሰልጣኝ ቶማስ ቱኸል ይህን የአዝቴካ ስታዲየም የከፍታ ፣ የደጋፊ ሁከትና ጩኸት ፈተና ለመወጣት የታክቲክ ለውጥ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ኳስ በመቆጣጠር ፣ የጨዋታውን ፍጥነት በማዘግየት ፣ ጉልበት በመቆጠብ እድል ሲገኝ ብቻ ለማጥቃት ይገባሉ ተብሏል።
እንግሊዝ በዚህ ስታዲየም በ1986ቱ አለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ በአርጀንቲና 2 ለ 1 ከተሸነፈች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ትጫወትበታለች። ለዘመናት የሚታወሰው የዲየጎ ማራዶና " የፈጣሪ እጅ ግብ " ለእንግሊዝ ሽንፈት ምክንያት መሆኑ ይታወሳል።
አርብ እለት ከብሪታኒያና ሜክሲኮኮ የወጡ መረጃዎች ዛሬ በሜክሲኮ ሲቲ አውሎ ንፋስና ጎርፍ የሚያስከትል የአየር ሁኔታ ሊከሰት እንደሚችል ስለተገመተ፣ ፊፋ የጨዋታ መርሃብ ግብር የማስተካከል እቅድ እንዳለው ቢነገርም ቀድሞ በተያዘለት ሰአት ይካሄዳል።
በሁሴን ግዛው

1 month ago