Logo
Getu Temesgen
‎መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከ2,900 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ
‎
‎#ethiopia | ​የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2,931 ተማሪዎችን በዛሬው እለት አስመርቋል።
‎
‎የትምህርት ገበታቸውን በስኬት አጠናቀው ለምረቃ ከበቁት የዘንድሮ ተመራቂዎች መካከል 849ኙ ሴቶች መሆናቸው
‎በምረቃው መርሐግብር ላይ ተገልጿል።
‎
‎​ዩኒቨርሲቲውን በዘንድሮ አመት 1,864 ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም 45 ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን ጨምሮ 939 ተማሪዎችን በሁለተኛ ዲግሪ አስመርቋል።
‎
‎ከተመራቂዎቹ ውስጥ 45 ተማሪዎች በሦስተኛ ዲግሪ (ፒኤችዲ) ሲሆኑ 83 የሚሆኑት ደግሞ በስፔሻሊቲ አጠናቀዋል።
‎
‎​በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፋና ሓጎስ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር የትምህርት ጥራትን ይበልጥ ለማረጋገጥ እና የተመራቂዎችን የፈጠራ ክህሎት ለማሳደግ የሚያስችል ሰፊ የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ መደረጉን ጠቁመው፣ ተመራቂዎቹ በተሰማሩበት የሥራ መስክ ኅብረተሰቡን በቅንነትና በትጋት እንዲያገለግሉ አሳስበዋል።

‎Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
‎
‎#getutemesgen #getu #ጌጡ

​#mekelleuniversity ​#graduation​#ethiopianuniversities​#highereducation

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.