Logo
SeledaPost
100 ኢትዮጵያውያን ነፃ የውጭ የትምህርት ዕድል ማግኘታቸውን የእስራኤል ኤምባሲ ገለጸ

የኢትዮጵያና እስራኤል የትብብር መስኮች ውስጥ አንዱ በሆነው የትምህርት ዕድል፣ በዚህ ዓመት 100 ተማሪዎች በመንግስት ለመንግስት በሚደረገው ግንኙነት ወደ እስራኤል ለትምህርት ማቅናታቸውን የእስራኤል ኤምባሲ ለአሐዱ ገልጿል።

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብረሃም ንጉሴ፤ ተማሪዎቹ በተለያየ መስክ ሙያ ሰልጥነውና ልምድን ቀስመው የሚመለሱባቸው ሁኔታዎች መኖራቸውን ገልጸዋል።

ከእነዚህም መካከል በመንግስት ለመንግስት በሚደረገው ግንኙነት፣ በእስራኤል የውጭ ግንኙነት ማዕቀፍ ውስጥ የሚሰጠው የትምህርት ዕድል አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በግብርና፣ ቴክኖሎጂ፣ ህክምና እንዲሁም በሰላምና ፀጥታ ዘርፎች የረጅም እና የአጭር ጊዜ ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆናቸውን የገለጹት አምባሳደሩ፤ ስልጠናው የሴቶች የአመራር ክህሎት እና የህፃናት ዕድገትንም የሚያካትት መሆኑን ጠቁመዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በግሉ ዘርፍ በሚደረግ ግንኙነት ባለሙያዎችን በተለያየ መንገድ በማሰልጠን ወደ ስራ የሚያስገቡበት ሁኔታ መኖሩን አንስተዋል። ለአብነትም "Save a Child's Heart" የተባለው ድርጅት በእስራኤል ሀገር ለአምስት ዓመታት ለአምስት የህክምና ባለሙያዎች የትምህርት ዕድል በመስጠት፣ አሁን ላይ በኢትዮጵያ በስፔሻሊስትነት ደረጃ እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

Seledadotio
Seledadotio
1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.