(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ ማዕከላዊ እዝ በባህረ ሰላጤው አካባቢ በነዳጅ ጫኝ መርከብ ላይ ኢራን ለፈጸመችው የድሮን ጥቃት አጸፋዊ ምላሽ ለመስጠት፣ የኢራን የሚሳኤል እና የድሮን ማከማቻ ስፍራዎች እንዲሁም የባህር ዳርቻ የራዳር ጣቢያዎች ላይ ኃይለኛ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል።
የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ በኤክስ ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፣ ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት መፈረሟንና አሜሪካም ይህንን ስምምነት ማክበሯን አስታውሰዋል። የመግባቢያ ሰነዱን አተገባበር በተመለከተ አለመግባባት ካላቸው ስልክ አንስተው መነጋገር እንደሚችሉ የገለጹት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፣ ለሚሰነዘርባቸው ማንኛውም የኃይል እርምጃ በኃይል ምላሽ እንደሚሰጡ አስጠንቅቀዋል።
በሌላ በኩል የኢራን አብዮታዊ ዘብ (IRGC) የአሜሪካን ጥቃት በጽኑ ያወገዘ ሲሆን፣ ዋሽንግተን እንደተለመደው የገባችውን ቃል አጥፍታለች ብሏል። የኢራን የባህር ኃይልም የአሜሪካ ጦር በሚገኝባቸው የቀጠናው ስፍራዎች ላይ ኢላማ አድርጎ ጥቃት መሰንዘሩን የገለጸው አብዮታዊ ዘቡ፣ ይህ ትንኮሳ የሚደገም ከሆነ የሚሰጠው አጸፋዊ ምላሽ ይበልጥ ሰፊ እንደሚሆን ዝቷል።
የኢራን ፓርላማ የብሔራዊ ደህንነት ኮሚቴ ኃላፊ ኢብራሂም አዚዚ በበኩላቸው በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለድርድር መርሆችም ሆነ ለተኩስ አቁም ስምምነቱ ምንም አይነት ቁርጠኝነት እንደሌላቸው በተግባር አሳይተዋል ሲሉ ወቅሰዋል። ኃላፊው የአሜሪካን የቅርብ ጊዜ ጥቃት፣ የተኩስ አቁም ስምምነቱን የጣሰ የእብሪት እርምጃ በማለት በጽኑ አውግዘውታል።

1 month ago