Logo
EBC
ቀጣይነት ያለው ውይይትና የጋራ ተነሳሽነት ለአፍሪካና ለኢምሬትስ ዘላቂ ብልፅግና እና ጥንካሬ አስፈላጊ ነው - አምባሳደር ሐደራ አበራ
***********************

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሐደራ አበራ ዛሬ በአዲስ አበባ በተካሄደው የ"ሂሊ ቀጣናዊ ውይይት - የአፍሪካ እትም 2026" መድረክ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

ፎረሙ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ከኢምሬትስ የስትራቴጂያዊ ጥናትና ምርምር ማዕከል እና ከአንዋር ጋርጋሽ የዲፕሎማሲ አካዳሚ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ነው።

ፖሊሲ አውጪዎችን፣ ዲፕሎማቶችን፣ የንግድ መሪዎችን እና ተመራማሪዎችን በአንድ ያሰባሰበው መድረክ፣ በአፍሪካ እና በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ መካከል ያለውን ትብብር ለማሳደግ ያለመ ነው።

አምባሳደር ሐደራ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ውስጥ ያላትን እያደገ የመጣ ሚና በዳሰሱበት ንግግራቸው፣ በመከባበር፣ በጋራ ብልፅግና እና በረጅም ጊዜ ቁርጠኝነት ላይ የተመሠረቱ አጋርነቶች ያላቸውን ጠቀሜታ አብራርተዋል።

በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ እና በዘላቂ ልማት ዘርፎች ትብብርን ማስፋት እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ቀጣይነት ያለው ውይይት እና የጋራ ተነሳሽነት ለአፍሪካም ሆነ ለኢምሬትስ ዘላቂ ብልፅግና እና ጥንካሬ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ባላት ስትራቴጂያዊ መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ የተነሳ ይህን የጋራ ራዕይ ለማራመድና የበኩሏን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆኗንም አምባሳደር ሐደራ ገልጸዋል።
#ethiopia #africa #uae #ebc

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.