(ዘ-ሐበሻ ዜና) የፀጥታው ምክር ቤት RSF የሚያደርገውን ጥቃት እንዲያቆም አሳሰበ፡፡ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ወይንም RSF በአል ኦቤድ አካባቢ ወታደራዊ ሀይሉን እያጠናከረ መሆኑን መስማቱን ገልፆ ይህም በከተማው ውስጥ ጥቃት ለመፈፀም መዘጋጀቱን እንደሚያመለክት አስረድቷል፡፡
ጨምሮም ሁኔታው የጅምላ ግድያን ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት ስላደረበት ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ጥቃቱን በአስቸኳይ እንዲያቆም አሳስቧል፡፡ መግለጫው በመቀጠልም ‹‹‹የምክር ቤቱ አባላት በኮርዶፋን ግዛት እየተባባሰ የመጣውን ግጭት ጨምሮ በሱዳን የቀጠለው ጦርነት አስከፊ የሆነውን የሰብአዊነት ሁኔታ የባሰ ያደርገዋል በሚል በጥልቅ አሳስቧቸዋል፡፡ በመሆኑም በአስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ ያቀርባሉ›› ብሏል፡፡ አስከትሎም ሁሉም ተፋላሚ አካላት ሲቪሎችን የመጠበቅና አለም አቀፍ ህጎችን የማክበር ግዴታ እንዳለባቸው ገልጿል፡፡
በአል ኦቢድ ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉና ሁለቱም ተፋላሚዎች ደግሞ በመላው አገሪቱ የሚያከናውኑት የድሮን ጥቃት እንዳሳሰበው የጠቀሰው ምክር ቤቱ በተፈፀሙ ሁሉም የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይ ምርመራ ተደርጎ አጥፊዎች ተጠያቂ እንዲሆኑም አሳስቧል፡፡
ሁለቱም ተፋላሚዎች ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ እንቅስቃሴ የመፍቀድ ግዴታ እንዳለባቸውም ገልፆ ይህ ጦርነት እንዲቀጥልና ሰላም እንዳይፈጠር ድጋፍ የሚያደርጉ የውጭ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ መልእክት አስተላልፏል፡፡ የፀጥታው ምክር ቤት ጨምሮም ለሱዳን ሉአላዊነት፣ ነፃነትና የግዛት አንድነት እውቅና እንደሚሰጥ ያረጋገጠ ሲሆን ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች የመሰረተው ትይዩ መንግስት ተቀባይነት እንደሌለው አስታውቋል፡፡

2 months ago