(ዘ-ሐበሻ ዜና) አየርላንድ 853,000 ዶላር አውጥታ 42 ደቡብ አፍሪካዊያንን ወደአገራቸው አባረረች፡፡ በደቡብ አፍሪካ ውስጥ መጤ ጠል ወይንም የዜኖፎቢያ ዘመቻ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህ ዘመቻም ዶክመንት የሌላቸው የውጭ አገር ዜጎች ከጁን 30 በፊት ደቡብ አፍሪካን ለቀው እንዲወጡ የሚል ማስጠንቀቂያ እየተላለፈ ነው፡፡ በሌላ በኩል አየርላንድ ደግሞ 42 ደቡብ አፍሪካዊያንን ከአገሯ አባራለች፡፡
የተባረሩትም ‹‹ያለ ዶክመንት እየኖሩ ነው›› በሚል ነው፡፡ አይሪሽ ታይምስ እንደዘገበው እነዚህ ደቡብ አፍሪካዊያን እንዲጠረዙ የተደረገው በፈቃደኝነት ወደአገራቸው እንዲመለሱ የቀረበላቸውን አማራጭ ባለመቀበላቸው ነው፡፡ እንደዘገባው የአየርላንድ ብሄራዊ ኢሚግሬሽን ቢሮ ሀሙስ እለት ባደረገው ዘመቻ 42ቱን ደቡብ አፍሪካዊያን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ በነጋታው በአውሮፕላን አሳፍሯቸዋል፡፡
9 ወንዶችን፣ 18 ሴቶችንና 15 ህፃናትን የያዘው ይህ አውሮፕላንም ትላንት ደቡብ አፍሪካ አርፏል፡፡ የአየርላንድ ኢሚግሬሽን ቃል አቀባይ ለጋዜጣው በሰጡት መግለጫ እነዚህን ደቡብ አፍሪካዊያን ወደአገራቸው ለመመለስ መንግስት በእያንዳቸው 20,087 ዶላር ወጪ ያደረገ መሆኑን ጠቅሰው ይህም 853,000 ዶላር እንደሚሆን አስታውቀዋል፡፡
ስደተኞቹን ለመመለስ ይህንን ያህል ገንዘብ ወጪ የሆነው እንደመጀመሪያ ግኝት መሆኑን ጠቅሰውም ደረሰኞች ሲሰበሰቡ ከዚህም ሊበልጥ እንደሚችል አስረድተዋል፡፡

2 months ago